የዋልያዎቹን ጨዋታ እነማን ይመሩታል

የዋልያዎቹን ጨዋታ እነማን ይመሩታል

ዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት የሚደረገውን የኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች በአህጉራችን እና በሌሎች የዓለም ክፍሎች እየተደረጉ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም በምድብ አንድ ከግብፅ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሴራሊዮን፣ ጊኒ ቢሳዎ እና ጂቡቲ ጋር ተደልድላ እስካሁን አምስት ጨዋታዎችን አከናውናለች። በእነዚህ አምስት የምድብ ጨዋታዎች ከሦስት ነጥብ በላይ ማስመዝገብ ያልቻለው ቡድናችን የምድቡ ግርጌ ላይ ከምትገኘው ጂቡቲ ጋር ዛሬ ሌሊት 6 ሰዓት ስድስተኛ ጨዋታውን ያከናውናል።

በኤል አብዲ ስታዲየም (ሞሮኮ) የሚከናወነውን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት ደቡብ አፍሪካዊው ባዲ ሉግዞሎ፣ በረዳትነት ደግሞ አንጎላዊው ሳንቶስ ጄርሰን ኢሚሊያኖ እና ደቡብ አፍሪካዊው ሞኮይና ጋራ እንዲሁም በአራተኛ ዳኝነት ከሲሼልስ የመጡት አሪሶል ኖሪስ አሮን ጎድፍሬ እንደሚመሩት ተረጋግጧል።

ከጨዋታው ጋር በተያያዘ ዜና ሱፐር ስፖርት በአፍሪካ 1 (227) ቻነሉ ፍልሚያውን በቀጥታ ለተመልካቾች እንደሚያስተላልፍ ታውቋል።