ሀዋሳ ከተማ በውሰት ወጣት ተጫዋች አስፈርሟል

ሀዋሳ ከተማ በውሰት ወጣት ተጫዋች አስፈርሟል

የአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረቱ ሀዋሳ ከተማ አንድ ተጫዋችን በውሰት ከከፍተኛ ሊጉ ክለብ የግሉ አድርጓል።

የሊጉን የሁለተኛውን ዙር ውድድር በአዲሱ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምሕረት ስር እየተመራ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች በሁለቱ የአቻ እና በአንዱ ደግሞ ድልን የተቀዳጀው ሀዋሳ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማስፈረም በሊግ ካምፓኒው የወጣው የገንዘብ መጠን የሚገድበው በመሆኑ ብቸኛ የውሰት ዝውውርን ለማድረግ በመገደዱ ለቀጣዮቹ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎቹ አንድ ተጫዋችን ወደ ስብስቡ አካትቷል።

ቡድኑን በውሰት የተቀላቀለው ተጫዋች ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ዳንኤል አበራ ነው። በኢትዮጵያ መድን የነበረውን ቆይታ አጠናቅቆ ከደደቢት ጋር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ “ሀ” ውድድር ላይ ድንቅ እንቅስቃሴን ሲያደርግ የታየው ተጫዋቹ በይፋ የፕሪሚየር ሊጉን ክለብ ሀዋሳን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።