በኢትዮጵያ የስፖርት ትጥቅ ኢንደስትሪ ውስጥ አዳዲስ ነገሮችን እያስተዋወቀ የሚገኘው ጎፈሬ “ኳሴ” የተሰኘውን ምርቱን እና አዲሱን የምርት አምባሳደሩን ዛሬ አመሻሽ አስተዋውቋል።
ዛሬ አመሻሽ በማሪዮት ኤክዜክዮቲቨ አፖርትመንት እና ሆቴል በተደረገው መርሃግብር “ኳሴ” የተሰኘውን የመጀመሪያ ሀገርኛ የኳስ ምርት እና ለዚህም ምርቱ የቀድሞው እግር ኳስ ተጫዋች ኃይሌ ካሴ(ኳሴ) መሾሙንም እንዲሁ ይፋ አድርጓል።
በመርሃግብሩ ጅማሮ የጎፈሬ መስራች እና ባለቤት አቶ ሳሙኤል መኮንን ስለስምምነቱ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በገለፃቸውም ኃይሌ ካሴ በራሱ ትልቅ ብራንድ መሆኑን አንስተው ከጎፈሬ ጋር በመጣመር ይህ ታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ምርት ማስተዋወቅ በመቻላቸው እጅጉን መደሰታቸውን ገልፀው በሂደት የተሳተፉትን አካላት በሙሉ አመስግነዋል።
በማስከተል የምርት አምባሰደር ስምምነቱ በኃይሌ ካሴ እና በጎፈሬ መስራች እና ባለቤት ሀሰን መሀመድ መካከል ከተፈረመ በኋላ “ኳሴ” የተሰኘችው የጎፈሬ ምርት የሆነችው ኳስም በይፋ ተዋውቃለች።
በመጨረሻም በዛሬው ዕለት በይፋ የተዋወቀችው “ኳሴ” የተሰኘችው እና የኃይሌ ፊርማ ያረፈባት ኳስ ለጨረታ ቀርባለች።