በመጨረሻው ሳምንት ከገጠማቸው ሽንፈት ለማገገም ወደ ሜዳ የሚገቡት ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከተማ የሚያገናኘው ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ካለው ወሳኝነት ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በሀያ ስምንት ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች በመጀመርያው ዙር የመጨረሻ አራት ሳምንታይ ያሳዩት ብቃት ማስቀጠል ተስኗቸዋል። በሁለተኛው ዙር በተካሄዱ አራት ጨዋታዎች በሦስቱ ሽንፈት አስተናግዶ በአንዱ ድል ያደረገው ቡድኑ በደረጃ ሰንጠረዡ አካፋይ መቀመጥ ቢችልም በስጋት ቀጠናው ካሉት ቡድኖች ያለው የጥብ ልዩነት ጥቂት ነው፤ ይህንን ተከትሎ በነገው ዕለት የሚያደርገው ጨዋታ ወሳኝነቱ ትልቅ ነው።
ባለፉት አራት የጨዋታ ሳምንታት ባስመዘገቡት ደካማ ውጤት ምክንያት ደረጃቸው ያሽቆለቆለው ኤሌክትሪኮች ዳግም ወደ ውጤት ጎዳና ለመመለስ በቀዳሚነት የማጥቃት አጨዋወታቸውን ማሻሻል ይኖርባቸዋል። ሦስት ድሎች እና አንድ የአቻ ውጤት ባስመዘገቡባቸው አራት ውጤታማ ሳምንታት ስምንት ግቦች ካስቆጠሩ በኋላ በመጨረሻዎቹ አራት መርሐ-ግብሮች አንድ ግብ ብቻ ያስቆጠሩት የአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ልጆች በነገው ጨምሮ በቀጣይ ጨዋታዎች የቀደመው የማጥቃት ጥንካሬያቸው መመለስ ግድ ይላቸዋል። ቡድኑ በነገው ዕለት ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት በሚያደርገው ጉዞ የሞት ሽረት ፍልምያ ያደርጋል ተብሎ የሚጠበቀው ሀዋሳ ከተማ እንደመግጠሙም የሚጠብቀው ፈተና በቀላል የሚታይ አይደለም።
በሀያ ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ሀዋሳ ከተማዎች ከነገው ዕለት ሙሉ ነጥብ ማግኘት የአንድ ደረጃ መሻሻል ያስገኝላቸዋል።
የመጀመርያው የከተማቸው ጨዋታ በኢትዮጵያ መድን ሽንፈት በማስተናገድ የጀመሩት ሀዋሳ ከተማዎች ከሦስት ሽንፈት አልባ ጨዋታዎች በኋላ በሊጉ መሪ ሽንፈት ብያስተናግዱም የቅርብ ሳምንታት ብቃታቸው ለክፉ የሚሰጥ አይደለም።
በ15ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አዳማ ከተማ ረፋድ ላይ ባከናወነው ጨዋታ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ደረጃው የሚያሻሽልበት ዕድል ያገኘው ቡድኑ የወጥነት ችግር የሚታይበት የአፈፃፀም ድክመቱን መቅረፍ ከጨዋታው አንዳች ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስችለዋል ተብሎ ይታመናል። ከኢትዮጵያ ቡናና ሀድያ ሆሳዕና ከመሳሰሉ ጠንካራ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ጥሩ የመከላከል መዋቅር የነበራቸው ሀይቆቹ ከተጋጣምያቸው የቅርብ ሳምንታት የማጥቃት አቅም አንፃር በመከላከሉ ረገድ ይፈተናሉ ተብሎ ባይገመትም በመጨረሻው ጨዋታ የነበራቸው ውስን የመከላከል ድክመት ማሻሻል ይኖርባቸዋል።
በኢትዮ ኤሌትሪክ በኩል ጉዳት ላይ የነበሩት አአብዱላዚዝ አማን እና በፍቃዱ አስረሳኸኝ ወደ ልምምድ መመለሳቸው ቢሰማም ለነገው ጨዋታ እንደማይደርሲ ሲታወቅ የተቀሩት የቡድኑ ተጫዋቾች ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ናቸው። በሀዋሳ ከተማ በኩል ተከላካዩ በረከት ሳሙኤል ከጉዳት ሲመለስ እሰራኤል እሸቱም በተመሳሳይ ከቅጣት ይመለሳል።
ቡድኖቹ በሊጉ 43 ግንኙነቶች ሲኖራቸው ኤሌክትሪክ 18 አሸንፋ ሀዋሳ 15 ጨዋታዎች ላይ ድል አድርጓል። 10 ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። ኤሌክትሪክ 65 ፣ ሀዋሳ ደግሞ 49 ጎሎችን አስቆጥረዋል።