ወልዋሎን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ የሚያሰለጥነው አሰልጣኝ ታውቋል

ወልዋሎን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ የሚያሰለጥነው አሰልጣኝ ታውቋል

አታኽልቲ በርኸ ከ13 ዓመታት በኋላ ወልዋሎን በዋና አሰልጣኝነት ይመራል።

ከቀናት በፊት ከአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ጋር የተለያዩትን ወልዋሎዎች እስከ ውድድር ዓመቱ ፍፃሜ ድረስ የሚያሰለጥነው አሰልጣኝ ታውቋል፤ በዚህ መሰረት በዓመቱ መጀመርያ ከበርካታ ጊዜያት በኋላ ወደ ቡድኑ ተመልሶ በምክትል አሰልጣኝነት ሲሰራ የቆየው አታኽልቲ በርሐ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆኗል።

ወልዋሎ በ2004 የብሔራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ላይ ሻምፒዮን እንዲሆን እና በሀገራዊ ውድድሮች እንዲሳተፍ ከረዳ በኋላ ለስድስት ዓመታት የወልዋሎ ሁለተኛ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ የሰራው አታኽልቲ በ2011 ሰሎዳ ዓድዋን ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከ13 ዓመታት በኋላ ዳግም የቢጫዎቹን ዋና አሰልጣኝነት መንበር ተረክቧል።