ኢትዮጵያዊው ተስፈኛ የአሜሪካውን ክለብ ተቀላቅሏል

ኢትዮጵያዊው ተስፈኛ የአሜሪካውን ክለብ ተቀላቅሏል

የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጫዋች በአሜሪካ አዲስ ክለብ አግኝቷል።

ባለፈው ዓመት መጨረሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና
ኢትዮጵያ ቡና በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ካደረጉት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ በኋላ ከቡድኑ ተለይቶ በሀገሪቱ የቆየው ተስፈኛው አማካይ አቤሴሎም ዘመንፈስ ሲያትል ከተማ ለሚገኝ ባላርድስ የተባለ ክለብ ፌርማውን አኑሯል።

በመቐለ ከተማ በሚገኙ የታዳጊ ቡድኖች ቆይታ ካደረገ በኋላ በቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ እና ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ተጫዋቹ ክለቡ ያዘጋጀለትን የሙከራ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ተከትሎ በሰሜን ምዕራብ ዲቪዥን USL ሊግ ሁለት ለሚሳተፈው ክለብ ፊርማውን አኑሯል።