የሊግ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎች የሚደረጉበት ቀን ይፋ ተደርጓል

የኢትዮጵያ ሊግ ዋንጫ ቀሪ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እና ቀጣይ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች የሚደረገበትን ቀን ፌዴሬሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ምክንያት በሩብ ፍፃሜው ከአርባምንጭ ጋር ጨዋታውን ማድረግ ያልቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ግንቦት 24 ቀን 2008 ይወታል፡፡ የሁለቱ አሸናፊም በግማሽ ፍጻሜው አዳማ ከተማን ይገጥማሉ፡፡ ሁለቱ ክለቦች ባለፈው የውድድር ዘመን በተመሳሳይ በሩብ ፍፃሜ ተገናኝተው ቅደስ ጊዮርጊስ በናትናኤል ዘለቀ ግሩም ግብ 1-0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከፕሪሚየር ሊጉ መጠናቀቅ ከ4 ቀናት በኋላ የሚካሄዱ ሲሆን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ/አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ ይጫወታሉ፡፡ ሰኔ 19 ደግሞ የፍፀሜው ጨዋታ ይካሄዳል፡፡
 
የጨዋታ መርሃ ግብሮች

ሩብ ፍፃሜ ፡ ግንቦት 24 ቀን 2008

11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ (አአ ስታድየም)

ግማሽ ፍጻሜ ፡ ሰኔ 16 ቀን 2008

(ጨዋታ 1)  09፡00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ (አአ ስታድየም)

(ጨዋታ 2)  11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ/አርባምንጭ ከተማ ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)

ፍጻሜ ፡ ሰኔ 19 ቀን 2008

10፡00 የጨዋታ 1 አሸናፊ ከ ጨዋታ 2 አሸናፊ (አአ ስታድየም)


የውድድሩ ስያሜ ‹‹የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ጥሎ ማለፍ ውድድር›› ነው፡፡ በዘገባዎቻችን ‹‹ሊግ ዋንጫ›› በሚል ስያሜ አሳጥረን የምንጠራው ለአፃፃፍ አመቺነት ነው፡፡ 

Leave a Reply