ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ደደቢት – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 ደደቢት

33′ ራምኬል ሎክ

72′ ምንተስኖት አዳነ

88′ አዳነ ግርማ


ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

 

90′ ጎድዊን ቺካ አዳነ ግርማን ቀይሮ ገብቷል።

 

88′ ጎል!!!

አዳነ ግርማ የጊዮርጊስን 3ተኛ ግብ አስቆጥሯል። ይህንንም ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው ሳላዲን ሰዒድ ነው።

 

80′ ዳዊት ፍቃዱ ያሻማውን ኳስ ሳኑሚ ሞክሮ ሮበርት ይዞበታል።

 

79′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

በኀይሉ አሠፋ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል።

 

76′ የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት

ተስሎች ሳይመን እና ሺመክት ጉግሳ ወጥተው ያሬድ ብርሃኑ እና ሳሙኤል ሳኑሚ ገብተዋል።

 

72′ ጎል!!!

ሳላዲን ሰዒድ በግራ በኩል አታሎ በመግባት የሰጠውን ኳስ ምንተስኖት አዳነ አስቆጥሯል።

 

66′ ምንተስኖት አዳነ ከርቀት የሞከረው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል።

 

64′ ተካልኝ ደጀኔ በሳላዲን ሰዒድ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ተመልክቷል።

 

58′ በኀይሉ አሠፋ ከሳጥን ውጪ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ይዞበታል።

 

56′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ራምኬል ሎክ ወጥቶ ምንያህል ተሾመ ገብቷል።

 

47′ በስታዲየሙ ዝናብ መጣል ጀምሯል ።

 

46′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል።

 

የመጀመሪያው አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ 1-0 መሪነት ተጠናቋል።

 

45′ አራት ደቂቃ የባከነ ሰዓት ተጨምሯል።

 

41′ ራምኬል ተጎዳሁ ብሎ ቢወድቅም ዳኛው ሰዓት ለመግደል ነው በሚል ቢጫ ካርድ አሳይተውታል።

 

39′ የምንተስኖት አዳነን የጭንቅላት ኳስ ግብ ጠባቂው ብርሃነ ይዞበታል።

 

33′ ጎል!!!

አዳነ ግርማ የመታው ፍፁም ቅጣት ምት በግብ ጠባቂው ሲመለስ ራምኬል ሎክ ኳሱን ወደ ግብ ቀይሮታል።

 

32′ ምኞት ደበበ ቢጫ ካርድ አይቷል። የደደቢት ተጫዋቾች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ።

 

31′ ምኞት ደበበ በሰራው ጥፋት አወዛጋቢ ፍፁም ቅጣት ምት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተሰጥቷል።

26′ ለሮበርት የህክምና ዕርዳታ ከተደረገለት በኃላ ጨዋታው ቀጥሏል።

 

23′ ዳዊት ፍቃዱ ከበረኛው ጋር ፊት ለፊት ቢገናኝም ሮበርት ኦዶንካራ ኳሱን ይዞበታል።

 

18′ ምንተስኖት አዳነ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ የመታውን ኳስ በረኛው ለጥቂት አውጥቶበታል።

 

15′ ጨዋታው በተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ቀጥሏል። ግልፅ የግብ አጋጣሚዎች ግን እስካሁን አልተመለከትንም።

 

8′ ብርሃኑ ቦጋለ ከርቀት የመታው ኳስ የግቡን ቋሚ መቶ ወጥቷል።

 

5′ ሳላዲን ሰዒድ ከአዳነ የተላከለትን ኳስ ወደ ጎል ቢመታም ግብ ጠባቂው በቀላሉ ይዞበታል።

 

2′ የደደቢቱ ሺመክት ጉግሳ በቀኝ መስመር በኩል በመግባት የመጀመሪያውን ሙከራ አድርጓል።

 

1′ ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አማካኝነት ተጀምሯል።

 


09:02 እሁድ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

09:00 ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተዋል።

 

08:30 አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ከ ብሄራዊ ቡድን ስንብት መልስ ለመጀመርያ ጊዜ በቅዱስ ጊዮርጊስ ረዳት አሰልጣኝነት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡ የደደቢቱ ረዳት አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሃዬ ባልታወቀ ምክንያት አይገኙም፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

14 አለማየሁ ሙለታ – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 3 መሃሪ መና

17 ራምኬል ሎክ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ – 7 በሃይሉ አሰፋ

19 አዳነ ግርማ – 10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች

23 ዘሪሁን ታደለ
4 አበባው ቡታቆ
ፍሬዘር ካሳ
20 ዘካርያስ ቱጂ
9 ምንያህል ተሾመ
16 ጎድዊን ቺካ
26 ናትናኤል ዘለቀ


የደደቢት አሰላለፍ

30 ብርሃነ ፍስሃዬ

 

29 ምኞት ደበበ – 14 አክሊሉ አየነው – 15 ጆን ቱፎር – 2 ተካልኝ ደጀኔ

 

19 ሽመክት ጉግሳ – 21 ኄኖክ ካሳሁን – 24 ተስሎች ሳይመን – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 10 ብርሃኑ ቦጋለ

 

17 ዳዊት ፍቃዱ

 

ተጠባባቂዎች

1 ምህረትአብ ገብረህይወት

23 ኄኖክ ኢሳያስ

99 ያሬድ ብርሃኑ

4 ያሬድ ዝናቡ

6 ብሩክ ተሾመ

9 ወግደረስ ታዬ

11 ሳሙኤል ሳኑሚ

Leave a Reply