የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል

ብላክ ሳተላይትስ በሚል ቅፅል ስም የሚታወቁት የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ ጋር ላለበት የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ትላንት ማታ 3:30 አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

29 አባላትን ይዞ የመጣው ብሄራዊ ቡድኑ 18 ተጫዋቾችን 8 የአሰልጣኞች ስታፍን እና 3 የአስተዳደር ባለሙያዎችን ይዟል፡፡ ማረፊያውን በአፋረንሲስ ሆቴል ሲያደርግ ዛሬ 10:00 ላይ ልምምዱን በሲኤምሲ ባንክ ሜዳ ያደርጋል፡፡

በአሰልጣኝ መስኡድ ዲዲ ድራማኒ የሚመራው ብሄራዊ ቡድኑ ከኢትዮጵያ ጋር ላለበት ጨዋታ ተጫዋቾችን የመረጠው ቀደም ብሎ ሲሆን ከካሜሮን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ መጫወትም ችሏል፡፡ ብላክ ሳተላይቶች በኪንግስሊ ናና ፎቢ አምበልነት ይመራል፡፡

የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ይህንን ይመስላል፡-

ክዋሜ ባህ (ኢንተር አላይስ) ፣ ቤንጃሚን አሴይዱ (ሞባይል ፎን ፒፕል) ፣ ኢማኑኤል ሎሞቲ (ድሪምስ) ፣ ኪንግስሊ ፎቢ (ራይት ቱ ድሪም) ፣ ዳንኤል አሞሃ (ሚዲአማ) ፣ ኒኮላስ ኦፖኩ (በርከም ቼልሲ) ፣ ኢሳኩ ኮንዳ (ዋ ኦል ስታርስ) ፣ አይዛክ ቱአም (ኢንተር አላይስ) ፣ ጆሴፍ ፕንትስል (ቴማ ዮዝ) ፣ መሃመድ አማንዶ (ዋ ኦል ስታርስ) ፣ ቻርለስ ቦአቴንግ (ዌስት አፍሪካን ፉትቦል አካዳሚ) ፣ ኢቫንስ ሜንሳ (ኢንተር አላይስ) ፣ ዳዉዳ መሃመድ (አሼንቴ ኮቶኮ) ፣ ኤኖች አዱ (ራይት ቱ ድሪም) ፣ ሚካኤል ኦቱ (ዩኒ ስታር አካዳሚ) ፣ ጆና ኦሳቡቲ (ቴማ ዮዝ) ፣ ጂዮፍሪ አቼምፖንግ (ራይት ቱ ድሪም) ፣ ሳርፖንግ (ሚዲአማ)

የኢትዮጵያ እና ጋና ከ20 አመት በታች ቡድኖች ጨዋታ እሁድ ግንቦት 14 ቀን 2008 በአዲስ አበባ ስታድየም ከቀኑ 10:00 ላይ ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply