“ስለ ኢትዮጵያ በቂ መረጃ የለንም” የጋናው አሰልጣኝ ዲዲ ድራማኒ

ዛምቢያ ለምታዘጋጀው የ2017 የአፍሪካ ከ20 ዓመት ዋንጫ ኢትዮጵያ በመጪው ዕሁድ ከጋና ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች፡፡

የጋና ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሲኤምሲ አከባቢ በሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር የልምምድ ሜዳ ትላንት 10:00 የመጀመሪያ ልምምዱን ሲሰሩ የብላክ ሳተላይትስ ዋና አሰልጣኝ ዲዲ ድራማኒ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በጨዋታው ዙሪያ ቆይታ አድርገዋል፡፡

 

ስለዝግጅት እና ስለብላክ ሳተላይቶች

ዝግጅታችንን የጀመርነው በማርች 14 ነው (ከአንድ ሳምንት በፊት)፡፡ ልምምዳችንን ወጥነት ይጎድለው ነበር፡፡ አብዛኛውን ጊዜው ከ20 ዓመት ብሄራዊ ቡድኖች አዲስ ነው የሚሆኑት፡፡ በብዛት ተጫዋቾቹ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ብድን በኩል አልፈው የሚመጡ ናቸው፡፡ በአፍሪካ በ17 ዓመት በታች እና በ20 ዓመት በታች ቡድኖች መካከል ሰፊ ልዩነት አለ፡፡ እኛም ይህንን ሰፊ ልዩነት ለማጥበብ እየሞከርን ነው፡፡ አብዛኞቹ ተጫዋቾቻችን በ17 ዓመት በታች ቡድን በኩል የመጡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ ከአካዳሚዎች፣ ከጋና ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ወጣት ቡድኖች እና ከዝቅተኛ ዲቪዚዮን የመጡ ናቸው፡፡ ዓላማችን ይህንን ቡድን ለዋናው ብሄራዊ ቡድን ብላክ ስታርስ ማሳደግ ነው፡፡

 

ስለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን

ስለተጋጣሚያችን የኢትዮጵያ ቡድን በቂ መረጃ የለንም፡፡ ይህ የማጣሪያ ውድድር ነው፡፡ የማጣሪያ ውድድር መሆኑ ደግሞ ተጋጣሚያችንን እንድናከበር እና ጠንካራ ዝግጅት እንድናደርግ ያስገድደናል፡፡

ስለእሁዱ ጨዋታ

እንደማስበው ከሆነ ነገሮችን አዎንታዊ በሆነ መንገድ እየተመለከትን ነው፡፡ ሁሌም የአሸናፊነትን ስሜትን ይዘን እንጫወታለን፡፡ ለእኛ ይህ የኢንተርናሽናል ጨዋታ ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሌም ጠንካራ የአሸናፊነት ስሜት አለን፡፡

ስላደረጓቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች

ጥሩ የሚሆነው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎቹን ከሜዳችን ውጪ ብናደርግ ነበር፡፡ አስፈላጊውን ኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ ለመውሰድ ይጠቅመን ነበር፡፡ ከካሜሮን፣ ቻይና እና ናሚቢያ ጋር ያደረግነው ጨዋታ በእጅጉ ጠቅሞናል፡፡ የእኛ ተጫዋቾች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ስላስቻለን የአቋም መፈተሸ ጨዋታዎቹ ማድረጋችን ጠቅሞናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *