ኢትዮጵያ U20 ከ ጋና U20 – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ 2-1 ጋና

4′ 9′ አሜ መሐመድ | 88′ ጆናህ ኦሳቡቲይ


ጨዋታው  በኢትዮጵያ ወጣት ቡድን 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

 

90+3′ አሜ የሞከረውን ኳስ የጋና ግብ ጠባቂ ይዞበታል።

 

90′ ተጨማሪ ሰዓት – 3 ደቂቃ

 

89′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

ዳዊት ማሞ ወጥቶ ሃብታሙ ገዛኸኝ ገብቷል።

 

88′ ጎል!!!

ጆናህ ኦሳቡቲይ ለጋና ግብ አስቆጥሯል።

 

78′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

ዘላለም ኢሳያስ ወጥቶ ኪዳኔ አሠፋ ገብቷል።

 

75′ የተጫዋች ለውጥ – ጋና

አይዛክ ትዉም ወጥቶ ጆሴፍ ፓንሲል ገብቷል።

 

71′ አቡበከር ሳኒ በጋና ሳጥን ውስጥ ቢወድቅም ዳኛው ጨዋታውን አስቀጥለዋል።

 

65′ አይዛክ ትዉም ከርቀት የመታው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።

 

63′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ

ሱራፌል አወል ወጥቶ አቡበክር ሳኒ ገብቷል።

 

61′ የጋናው ሚካኤል ኦቱ የጨዋታውን የመጀመሪያ ቢጫ ካርድ አይቷል።

 

53′ ኦሳቡቴይ ከጠባብ አንግል የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቷል።

 

የተጫዋች ለውጥ – ጋና

ኢቫንስ ሜንሳህ እና ሞስስ ሳርፖንግ ገብተው ቻርልስ ቦአቴንግ እና ኢማኑኤል ላሞቴይ ወጥተዋል።

 

46′ ሁለተኛው ግማሽ ተጀምሯል።

 

የመጀመሪያው ግማሽ በኢትዮጵያ ወጣት ቡድን 2-0 መሪነት ተጠናቋል።

 

45′ 2 ደቂቃ የባከነ ሰዓት ተጨምሯል።

 

31′ ኦሜ መሐመድ ከግብ ጠባቂው ጋር 1 ለ 1 ቢገናኝም ከጨዋታ ውጪ በሚል ተቋርጧል።

 

23′ ዳውዳ መሐመድ ከርቀት የመታው ኳስ ከአግዳሚው በላይ ወጥቷል።

 

13′ ዳዊት ማሞ ከኦሜ ጋር በጥሩ ቅብብል ካለፈ በኃላ ወደጎል ሞክሮ ወደላይ ወጥቶበታል።

 

10′ የጋናው ሚካኤል ኦቱ ከርቀት ሞክሮ ወደውጪ ወጥቶበታል።

 

9′ ጎል!!

ኦሜ መሐመድ በድጋሚ የጋናው ተከላካይ አይዛኩ ኮንዳ ስህተትን በመጠቀም ሁለተኛ ጎል አስቆጥሯል።

 

4′ ጎል!!!

ኦሜ መሐመድ ሱራፌል አወል ከጋና ተከላካይ የነጠቀውን ኳስ አስቆጥሯል።

 

1′ ጨዋታው በኢትዮጵያ ወጣት ቡድን በኩል ተጀምሯል ።

 


09:55 የሁለቱም ቡድኖች ብሔራዊ መዝሙር ተዘምሯል።

09:50 ተጫዋቾቹ ወደ ሜዳ  እየገቡ ይገኛሉ።

 

የኢትዮጵያ አሰላለፍ
1 ተክለማርያም ሻንቆ

7 ደስታ ደሙ – 2 ሀይደር ሙስጠፋ – 6 ተስፋዬ ሽብሩ – 3 ዳንኤል ራህመቶ

16 ዘላለም ኢሳያስ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ(አምበል) – 11 ዳዊት ተፈራ – 17 ዳዊት ማሞ

10 ሱራፌል አወል – 9 አሜ መሃመድ

ተጠባባቂዎች
12 ምንተስኖት የግሌ
18 ሀብታሙ ገዛኸኝ
4 ተመስገን አዳሙ
15 ሚካኤል ለማ
8 እንየው ካሳሁን
5 ኪዳኔ አሰፋ
14 አቡበከር ሳኒ

የጋና አሰላለፍ
1 ክዋሜ ባህ

17 ኢኖች አዱ – 3 ጂኦፍሬይ አቼምፖንግ – 2 ዳንኤል አሞሃ – 15 ኢሳኩ ኮንዳ

13 ሚካኤል ኦቱዎ – 8 አይዛክ ትዉም – 14 ኢማኑኤል ሎሞቲ – 18 ጆናታን ኦሳቡቲ

7 ቻርልስ ቦአቴንግ – 10 ዳውዳ መሃመድ (አምበል)

ተጠባባቂዎች
9 ጆሴፍ ፔንሲል
11 ኢቫንስ ሜንሳህ
12 ሞሰስ ሳርፖንግ
6 ኒኮላስ ኦፖኩ
16 ቤንጃሚን አሲዱ
5 ኪንግስሌይ ፎቢ
4 መሃመድ አማንዶ

 

1 Comment

Leave a Reply