ደደቢት አሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊትን አሰናበተ

በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ደደቢት ዋና አሰልጣኙን ለማሰነ፡ናበት መወሰኑን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡ ክለቡ ግን እስካሁን ይፋዊ ማረጋገጫ አልሰጠም፡፡

በአመቱ መጀመርያ የከፍተኛ ሊጉን ክለብ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለቀው ለደደቢት የፈረሙት አሰልጣኝ ጌታቸው ክለቡ በአንደኛው ዙር 2ኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ቢረዱትም በሁለተኛው ዙር ካደረጋቸው 8 ጨዋታዎች በ6ቱ ሽንፈት አስተናግደዋል፡፡ ወደ 8ኛ ደረጃም ተንሸራተዋል፡፡

ደደቢት ባለፈው ሳምንት ረዳት አሰልጣኙ ዳንኤል ፀሃዬን ማሰናበቱ የሚታወስ ሲሆን የተስፋ ቡድኑ አሰልጣኝ ኤልያስ ወይም የቴክኒክ ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት አስራት ሃይሌ በጊዜያዊነት አሰልጣኝ ኝነቱን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Leave a Reply