ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ (ደቡብ-ምስራቅ ዞን) ፡ ሀዋሳ ከተማ የዞኑ ቻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል

ሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንት እድሜ ብቻ የቀረው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሁድ ሲካሄዱ ሀዋሳ ከተማ የዞን ቻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

ሀዋሳ ላይ ተከታዩ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው መሪው ሀዋሳ ከተማ 3-1 አሸንፏል፡፡ የሀዋሳ ከተማን የድል ግቦች አዲስ ንጉሴ ፣ አይናለም አሳምነው እና ትብለጽ አፅብሃ ሲያሰቆጥሩ ተራማጅ ተስፋዬ የሲዳማ ቡናን ብቸኛ ግብ አስቆጥራለች፡፡ ድሉን ተከትሎ ሀዋሳ ከተማ 22 ነጥቦች በመሰብሰብ የዞኑ ቻምፒየንነትን አንድ ጨዋታ እየቀረው ማረጋገጥ ችሏል፡፡

ቅዳሜ እለት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን አስተናገዶ ካለ ግብ 0-0 ተለያይቷል፡፡

ትላንት አዳማ ላይ በተደረገው የአዳማ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ አዳማ ከተማ 1-0 አሸንፏል፡፡ የባለሜዳዎቹን ብቸኛ የድል ግብ በጨዋታው መገባደጃ ከመረብ ያሳረፈችው ስንታየሁ ማቲዎስ ናት፡፡

PicsArt_1464016618309

የመጨረሻ ሳምንት (10ኛ ሳምንት) ጨዋታዎች

እሁድ ግንቦት 21 ቀን 2008

09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (አርባምንጭ)

09፡00 ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከ ሀዋሳ ከተማ (አሰላ)

09፡00 ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ (ይርጋለም)

1 Comment

Leave a Reply