ሴቶች ፕሪሚር ሊግ፡ ዳሽን ቢራ ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፉን ያረጋገጠ 7ኛው ክለብ ሆኗል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት ሲጀምር በዛሬው እለት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡ ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎችም ይቀጥላል፡፡

በአዲስ አበባ ስታድየም 09፡00 ላይ ሙገር ሲሚንቶን የገጠመው ዳሽን ቢራ 2-0 በማሸነፍ ወደ ማጠቃለያው ውድድር ማለፉን አረጋግጧል፡፡ የዳሽን ቢራን የድል ግቦች ጥሩወርቅ ወዳጆ በመጀመርያው አጋማሽ ፣ ፋጡማ አሊ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ከ16 ጨዋታ 32 ነጥቦች የያዘው ዳሽን ቢራ ከመካከለኛው ዞን ወደ ማጠቃለያው ዙር ያለፈ 5ኛው ቡድን ሆን ችሏል፡፡

11፡00 ላይ ቅድስት ማርያምን የገጠመው ደደቢት ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 3-0 አሸንፎ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ የደደቢትን የድል ግቦች ሎዛ አበራ ፣ መስከረም ካንኮ እና በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ያሳየችው ሰናይት ቦጋለ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ከ16 ጨዋታ አንድ ሽንፈት ብቻ አስመዝግቦ ሁሉንም በድል የተወጣው ደደቢት በ45 ነጥቦች ዞኑን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

ትላንት በተደረገው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ልደታን 2-0 አሸንፏል፡፡ የቡናን የድል ግቦች ስራ ይርዳው እና ቁምነገር ካሳሁን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

የ4 ሳምንታት እድሜ ብቻ በቀረው የመካከለኛ-ሰሜን ዞን ወደ ማጠቃለያው ውድድር 5 ክለቦች ማለፋቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የቀረውን አንድ ቦታ ለማግኘት ከእቴጌ በቀር ሁሉም ተስፋ ቢኖረውም 22 ነጥብ የያዘው ኤሌክትሪክ እና 16 ነጥብ የያዘው ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ የተሻለ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

PicsArt_1464114495041

ማስታወሻ

– በ16ኛው ሳምንት ኤሌክትሪክ ከሙገር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ለሌላ ቀን በመተላለፉ አልተደረገም፡፡

– የ18ኛው ሳምንት ሊደረጉ የነበሩት ሁሉም ጨዋታዎች አአ ስታድየም ለኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ጨዋታ እና ዝግጅት በመያዙ ለሌላ ጊዜ ተዘዋውረዋል፡፡

– 10 ክለቦች የሚከፈሉበት የፕሪሚየር ሊጉ ማጠቃለያ ውድድር ከሰኔ 14 ጀምሮ በሀዋሳ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡ ከመካከለኛው-ሰሜን ዞን 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ ዞን 4 ክለቦች ወደ ማጠቃለያው ዙር ያልፋሉ፡፡

– ሀዋሳ ከተማ (የዞን ቻምፒዮን መሆን አረጋግጧል) ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ደደቢት ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ዳሽን ቢራ እና መከላከያ ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ ማለፋቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1464115021628

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *