የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾችን መለየት ጀምሯል

በቀጣዩ አመት በማዳጋስካር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ17 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሰኞ እለት ዝግጅት ጀምሯል፡፡

ተጨዋቾችን ለመለየት በ40 ተጨዋቾች የተጀመረው ዝግጅት ዛሬ ረፋድ ላይ ከ50 በላይ ተጫዋቾችን ሁለት ቦታ ከፍሎ በማጫወት ብቃታቸውን የመለየት ስራ ቀጥሏል፡፡

ለኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን የተጠሩት ተጫዋቾች በየክለባቸው ጨዋታ ያላቸው በመሆኑ ተጫዋቾች የመለየት ስራው ለጥቂት ቀናት የማይኖር ሲሆን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በየቀኑ በሚደረግ እንቅስቃሴ የመምረጥ ስራው የሚገባደድ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ።

PicsArt_1464262061098

የአሰልጣኝ አጥናፉ ረዳቶች

አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ረዳቶቻቸውን የመረጡ ሲሆን የንግድ ባንክ ከ17 አመት በታች አሰልጣኝ ጣሰው በረዳት አሰልጣኝነት ፣ የዳሽን ቢራው የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ አዳሙ ኑመሮ ደግሞ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

 

ተጨማሪ ተጫዋቾች

ለ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በመጀመርያ ጥሪ የደረሳቸው 40 ተጫዋቾች ቢሆኑም ከወዲሁ ተጨማሪ ተጫዋቾች ተካተው ስብስቡ ከ50 በላይ ሆኗል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናትም ተጨማሪ ተጫዋቾች ከደቡብ-ምስራብ ዞን እና ከክልሎች እንደሚመለመሉ አሰልጣኝ አጥናፉ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

” ተጨማሪ የሚመጡ ተጫዋቾች ይኖራሉ፡፡ የደቡብ ምስራቅ ከ17 አመት በታች ውድድር ቅዳሜና እሁድ የሚደረጉ ጨዋታዎችን ተመልክተን ምርጫ የምናካሂድ ሲሆን ከቤኒሻንጉል ፣ ድሬዳዋ እና ጋምቤላ ያየናቸውን ተጫዋቾች ከሰኞ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት እናያቸዋለን፡፡ በአጠቃላይ እነዚህን አሰባጥረን እንመለከትና በዚህ ወር መጨረሻ 25 ተጨዋቾችን በመያዝ በተጠናከረ መልኩ ለጨዋታው ዝግጅታችን እንጀምራለን፡፡ ”

PicsArt_1464261980575

የእድሜ ጉዳይ

አሰልጣኝ አጥናፉ የእድሜ ምርመራው ከወዲሁ እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል፡፡

“ከተጨዋቾች ምርጫ ጋር ጎን ለጎን በዚህ ሁለት ቀን ያየናቸውን ጥሩ አቅም ያላቸውን 24 ተጫዋቾች ከወዲሁ የMRI ምርመራ እንዲያደርጉ ልከናል፡፡ እኛ እዚህ አቅማቸውን ብናይ ኀላ ላይ መስፈርቱን ካላለፉ አስቸጋሪ ስለሚሆን MRI ን የሚያልፉ 25 ተጨዋቾችን የምንይዝ ይሆናል፡፡” ብለዋል፡፡

 

Leave a Reply