የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡
ሀዋሳ ከተማ ባለፈው ሳምንት የዞኑ ቻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ወደ ማጠቃለያው ውድድር የሚያልፉ ቀሪ ሁለች ቡድኖች በመጨረሻው ሳምንት ጨዋታዎች ይለያሉ፡፡
በደረጃ ሰንጠረዡ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃ የሚገኙት ድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ እርስ በእርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ድሬዳዋ አቻ ውጤት ወደ ማጠቃለያው ለማለፍ በቂው ሲሆን አርባምንጭ ከተማ ማሸነፍ ካልቻለ የተከታዮቹን ውጤት ለመጠበቅ ይገደዳል፡፡
በሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኘው ጥሩነሽ ዲባባ በሌሎች ውጤች ላይ የተመሰረተ ተስፋ ይዞ ሀዋሳ ከተማን ሲያስተናግድ አዳማ ከተማ ወደ ይርጋለም ተጉዞ ሲዳማን ይገጥማል፡፡ አዳማ 5ኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ እርስ በእርስ የሚጫወቱ በመሆናቸው ካሸነፈ ወደ ማጠቃለያው ማለፉን ያረጋግጣል፡፡
የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች
እሁድ ግንቦት 21 ቀን 2008
10:00 አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ (አርባምንጭ)
10:00 ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ከ ሀዋሳ ከተማ (አሰላ)
10:00 ሲዳማ ቡና ከ አዳማ ከተማ (ይርጋለም)
ፎቶ – ሀዋሳ ከተማ (ከ Hawassa Kenema የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ)