ከፍተኛ ሊግ ፡ መሪዎቹ ከተከታዮቻቸው ልዩነታቸውን ያሰፉበትን ድል አስመዝግበዋል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 18ኛ ሳምንት 15 ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ በሁለቱም ምድቦች አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ክለቦች አሸንፈው ከተከታዮቻቸው ያላቸውን የነጥብ ልዩነት አስፍተዋል፡፡

መልካ ቆሌ ላይ ወልድያ አስፈሪ ግስጋሴ በማድረግ መሪዎቹን የተጠጋው ኢትዮጵያ መድንን አስተናግዶ 2-0 አሸንፏል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከተማ ወደ ኮምቦልቻ ተጉዞ በሙሉቀን ታሪኩ ግብ ወሳኝ 3 ነጥብ ይዞ ተመልሷል፡፡

በደረጃ ሰንጠረዡ ከ3-6ኛ ላይ የሚገኙት መቀለ ከተማ ፣ መድን ፣ አውስኮድ እና ሱሉልታ ከተማ ነጥብ መጣላቸውን ተከትሎ ወልድያ እና ፋሲል የፕሪሚየር ሊግ ግስጋሴያቸውን አሳምሮላቸዋል፡፡

በምድብ ለ መሪው ጅማ አባ ቡና በጅማ ደርቢ ጅማ ከተማን አሸንፏል፡፡ ተከታዩ አአ ከተማም ከግሩም እንቅስቃሴ ጋር ናሽናል ሴሚንት ላይ ግማሽ ደርዘን በማስቆጠር አሸንፏል፡፡

ጅማ አባ ቡና እና አአ ከተማ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀራቸው ከተከታዮቻቸው ርቀው መገስገሳቸውን ቀጥለዋል፡፡

ከአስከፊ አጀማመር በኀላ በአስፈሪ አቋም ላይ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ዛሬም ከግማሽ ደርዘን በላይ ግብ በማስቆጠር ፌዴራል ፖሊስን 7-0 አሸንፏል፡፡ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ደቡብ ፖሊስ ተጋጣሚዎቹ ላይ 19 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡


የ18ኛ ሳምንት ውጤቶች እና ግብ አግቢዎች ይህን ይመስላሉ፡-

ምድብ ሀ

ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት 0-0 ሱሉልታ ከተማ

አማራ ውሃ ስራ 2-2 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
ጅላሎ ሻፊ ፣ አቤል ወልዱ | አቤል ወልዱ (በራሱ ግብ ላይ ፣ አብዱሰላም

መቀለ ከተማ 0-0 ሙገር ሲሚንቶ

ወሎ ኮምቦልቻ 0-1 ፋሲል ከተማ
ሙሉቀን ታሪኩ

ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን 1-0 አአ ፖሊስ
እሱባለው አንለይ

አክሱም ከተማ 1-0 ቡራዩ ከተማ
ክብሮም አፅብሃ

ወልድያ 2-0 ኢትዮጵያ መድን
እዮብ ወልደማርያም ፣ ሀብታሙ ገብረእግዚአብሔር

ባህርዳር ከተማ 0-0 ሰበታ ከተማ

PicsArt_1464584489886ምድብ ለ

ሻሸመኔ ከተማ 2-1 ጂንካ ከተማ
መሃመድ አሊ ፣ ፀጋ ጎሳዬ | ኪዳነማርያም

ደቡብ ፖሊስ 7-0 ፌዴራል ፖሊስ
ምስጋናው ወልደዮሃንስ (2) ፣ ወንድሜነህ አይናለም (2) ፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ (2) ፣ ሙሉነህ

ጅማ ከተማ 0-1 ጅማ አባ ቡና
ተመስገን

ድሬዳዋ ፖሊስ 1-1 ሀላባ ከተማ
አቤል ግርማ | አዩብ በቀታ

ወራቤ ከተማ 2-0 ነገሌ ቦረና
ፈድሉ ሃምዛ (2)

አርሲ ነገሌ 3-0 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
አገኘሁ ልኬሳ (2) ፣ ምትኬ ጌታቸው

አዲስ አበባ ከተማ 6-0 ናሽናል ሴሜንት
ሃይሌ እሸቱ (2) ፣ ሃይለየሱስ መልካ ፣ ዳዊት ማሞ ፣ ሙሃጅር መኪ ፣ እንየው ካሳሁን

እሁድ ግንቦት 21 ቀን 2008 

ነቀምት ከተማ 1-0 ባቱ ከተማ

ማንያዘዋል ጉዳዩ

PicsArt_1464584416495


7 Comments

  1. The premier league must increase its number to 16 so that two clubs of each category of the higher league must be involved in the premier league in 2009 E.C

    Woldya!!!

  2. Please Soccerethiopia.net inform us full Fixtures of higher league competition.

  3. ቢመችሽም ባይመችሽም አንዴ መተናል አንለቅሽም ምንግዜም ወልድያ

Leave a Reply