ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፡ የደቡብ-ምስራቅ ዞን ዛሬ ሲጠናቀቅ ድሬዳዋ እና አርባምንጭ አላፊዎቹን ክለቦች ተቀላቅለዋል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ-ምስራቅ ዞን ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ ድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማም ወደ ማጠቃለያው ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ቀደም ብሎ ቻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው ሀዋሳ ከተማ ወደ አሰላ ተጉዞ በጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ 1-0 ተሸንፏል፡፡ በሌሎች ውጤት ላይ የተመሰረተ የማለፍ ተስፋ የነበረው ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ድል ቢቀናውም አርባምንጭ እና ድሬዳዋ ነጥብ በመጋራታቸው ሳያልፍ ቀርቷል፡፡

ወደ ይርጋለም የተጓዘው አዳማ ከተማ በሲዳማ ቡና 4-1 ተሸንፏል፡፡ አዳማ ከተማ ጨዋታውን በድል ቢያጠናቅቅ ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ ማለፉን ያረጋግጥ ነበር፡፡

አርባምንጭ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ካለግብ አቻ ተለያይተው ወደ ማጠቃለያው ውድድር ተያይዘው አልፈዋል፡፡

ከደቡብ-ምስራቅ ዞን ወደ ማጠቃለያ ዙር ያለፉ ክለቦች
ሀዋሳ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ

የመጨረሻው ሳምንት ውጤቶች እና ግብ አግቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

ሲዳማ ቡና 4-1 አዳማ ከተማ
ተራማጅ ተስፋዬ ፣ አይዳ ኡስማን ፣ አረጋሽ ፀጋ ፣ ትርሲት መገርሳ | አብነት ጎበና

አርባምንጭ ከተማ 0-0 ድሬዳዋ ከተማ

ጥሩነሽ  ዲባባ 1-0 ሀዋሳ ከተማ
ናርዶስ ጌትነት

የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1464539069240

*የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በ10 ክለቦች መካከል በሀዋሳ አስተናጋጅነት ከሰኔ 14 ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን 9 ክለቦች (4 ከደቡብ-ምስራቅ ፣ 5 ከመካከለኛ-ሰሜን) ወደ ማጠቃለያው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

Leave a Reply