ወደ ሌሶቶ የሚያመሩ 18 ተጫዋቾች ታውቀዋል ፤ ጌታነህ ቡድኑን በአምበልነት ይመራል

በ2017 የጋቦን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በመጪው እሁድ ከሌሶቶ ብሄራዊ ቡድን ጋር ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡

አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ 7 ተጫዋቾች በመቀነስ ወደ ሌሶቶ ይዘዋቸው የሚጓዛቸውን ተጫዋቾች ይፋ አድርገዋል፡፡

ሳላዲን ሰኢድ በጉዳት ፣ ስዩም ተስፋዬ በፓስፖርት ጉዳዮች ምክንያት ወደ ሌሶቶ እንደማይጓዙ ከተረጋገጡት መካከል ናቸው፡፡

ከ25 የተጫዋቾች ስብስብ መካከል የተቀነሱት ሌሎችተጫዋቾች ሳምሶን አሰፋ ፣ አዲስ ተስፋዬ ፣ ኤፍሬም ወንድወሰን እና ሙሉአለም መስፍን ናቸው

ሳላዲን እና ስዩም ከቡድኑ ውጪ በመሆናቸው ዋልያዎቹ በሌሶቶው ጨዋታ ላይ አዲስ አምበል ይዘው ይገባሉ፡፡ አሰልጣኝ ገብረመድህን ከሳላዲን እና ስዩም በመቀጠል ጌታነህ ከበደ 3ኛ አምበል መሆኑን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

የ18 ተጫዋቾች ዝርዝር ይህንን ይመስላል፡-


ግብ ጠባቂዎች

ጀማል ጣሰው (መከላከያ) ፣ አቤል ማሞ (ሙገር ሲሚንቶ)


ተከላካዮች

አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አብዱልከሪም መሀመድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አንተነህ ተስፋዬ (ሲዳማ ቡና) ፣ ያሬድ ባየህ (ዳሽን ቢራ)


አማካዮች

ሽመልስ በቀለ (ፔትሮጄት) ፣ ኤፍሬም አሻሞ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ፣ አስራት መገርሳ (ዳሽን ቢራ) ፣ ታደለ መንገሻ (አርባምንጭ ከተማ) ፣ ሽመክት ጉግሳ (ደደቢት) ፣ ምንተስኖት አዳነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጋቶች ፓኖም (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ኤልያስ ማሞ (ኢትዮጵያ ቡና)


አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ፕሪቶርያ ዩኒቨርሲቲ) ፣ ታፈሰ ተስፋዬ (አዳማ ከተማ) ፣ ዳዊት ፍቃዱ (ደደቢት)


የስዩም ተስፋዬ የፓስፖርት ጉዳይ ነገ ከመጓዛቸው በፊት ከተጠናቀቀ 19ኛ ተጫዋች ሆኖ እንደሚጓዝ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ የፓስፖርት ጉዳይ ያላለቀለት ደስታ ዮሃንስ ጉዳይ ከተጠናቀቀና የስዩም ጉዳይ ካልተሳካ 19ኛ ተጫዋች ሆኖ ይጓዛል ተብሏል፡፡


 

4 Comments

  1. ሳላዲን አለመኖሩ አስጨንቆኛል።
    መልካም እድል!!

Leave a Reply