ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ : ደደቢት የዞኑ ቻምፒዮን ለመሆን ተቃርቧል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ-ሰሜን ዞን 20ኛ ሳምንት 3 ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው ደደቢት ፣ ንግድ ባንክ እና ሙገር ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ወደ ጎንደር ያመራው ደደቢት ዳሽን ቢራን በሎዛ አበራ 2 ግቦች ታግዞ 2-0 አሸንፏል፡፡ ከ17 ጨዋታ 48 ነጥቦች የሰበሰበው ደደቢት ቀጣዩን ጨዋታ በድል ካጠናቀቀ የመካከለኛው-ሰሜን ዞን ቻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሙገር ሲሚንቶ ኢትዮጵያ ቡናን በመሰሉ አበራ ግቦች 2-0 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሳሳይ እቴጌን 2-0 አሸንፏል፡፡


ማክሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2008


ዳሽን ቢራ 0-2 ደደቢት
ሎዛ አበራ (2)

ኢትዮጵያ ቡና 0-2 ሙገር ሲሚንቶ
መሰሉ አበራ (2)

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-0 እቴጌ
ብሩክታዊት ግርማ (ፍቅም) ፣ ብዙሃን እንዳለ


ረቡዕ ግንቦት 24ቀን 2008


09:00 ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ  ከ ልደታ ክ/ከተማ (አአ ስታድየም)

11:30 መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (አአ ስታድየም)


PicsArt_1464722980990


ማስታወሻ


– የዞኑ ውድድር ሊጠናቀቅ ይህን ሳምንት ጨምሮ የ4 ሳምንት ጨዋታዎች ይቀራሉ፡፡

– ከዚህ ዞን ለማጠቃለያ ውድድር የሚያልፉ ክለቦች 6 ናቸው፡፡ 5 ክለቦች (በሃምራዊ ቀለም የተፃፉት) ከወዲሁ ማለፋቸውን ሲያረጋግጡ በቀይ ቀለም የተፃፉት ደግሞ ወደ ማጠቃለያው እንደማያልፉ ያረጋገጡ ናቸው፡፡ ኤሌክትሪክ ቀሪዋን አንድ ቦታ ለመያዝ ሲቃረብ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ጠባብ የማለፍ ተስፋ አለው፡፡

– የማጠቃለያ ውድድሩ በሃዋሳ ከሰኔ 14 እስ 30 ይካሄዳል፡፡ ከመካከለኛው-ሰሜን ዞን 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ 4 በድምሩ 10 ክለቦች ይሳተፋሉ፡፡


 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *