ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ፡ መከላከያ እና ልደታ ድል ሲቀናቸው ቅድስት ማርያም ወደ ማጠቃለያው የማለፍ ተስፋውን አጨልሟል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ-ሰሜን ዞን 20ኛ ሳምንት ቀሪ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደው መከላከያ እና ልደታ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ ሽንፈት አጋጥሞት ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ የመግባት ተስፋው ጨልሞበታል፡፡

በ9፡00 ላይ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲን የገጠመው ልደታ ክፍለከተማ 1-0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ የልደታን የድል ግብ ከመረብ ያሳረፈችው ፍጹም ኪሮስ በፍፁም ቅጣት ምት ነው፡፡ ጨዋታው በቂ የግብ እድሎች ባይስተናገዱበትም በሁለቱም ቡድኖች በኩል ድንቅ እንቅስቃሴ ፣ የኳስ ፍሰት እና የተጫዋቾች የግል ክህሎቶች ታይተውበታል፡፡

በ2ኛው ዙር ውጤቱ ያሽቆለቆለው ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ 16 ነጥቦች ላይ ረግቶ ወደ ማጠቃለያው ዙር የማለፍ ተስፋው ጨልሟል፡፡ ኤሌክትሪክ በቀጣዩ ሳምንት 1 ነጥብ ካገኘ ወደ ማጠቃለያ ዙር ማለፉን ያረጋግጣል፡፡

PicsArt_1464810665025

11፡30 ላይ መከላከያ ቅዱስ ጊዮርጊስን ሁለት ጊዜ ከኋላ ተነስቶ ድል አድርጓል፡፡ ከአመቱ ምርጥ ጨዋታዎች አንዱ የሚያሰኝ ድንቅ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሄለን ሰይፉ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ ቢሆንም የምስራች ላቀው ከቀኝ መስመር የተገኘውን ቅጣት ምት በግሩም ሁኔታ አስቆጥራ የመጀመርያው አጋሽ 1-1 ተጠናቋል፡፡ የሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ተቀይራ ወደ ሜዳ የገባችው ሜሮን አብዶ በጥሩ ሁኔታ ተመስርቶ የመጣውን ኳስ ከርቀት በመምታት ግሩም ግብ አስቆጥራ ቅዱስ ጊዮርጊስን በድጋሚ መሪ አድርጋለች፡፡

ከግቡ መቆጠር በኋላ ጫና ፈጥረው የተንቀሳቀሱት መከላከያዎች በመጨረሻም ሰምሮላቸው ምስር ኢብራሂም ባስቆጠረቻቸው ተከታታይ ግቦች 3-2 በሆነ ማሸነፍ ችለዋል፡፡


የ20ኛ ሳምንት ውጤቶች

ማክሰኞ ግንቦት 23 ቀን 2008

ዳሽን ቢራ 0-2 ደደቢት
ሎዛ አበራ (2)

ኢትዮጵያ ቡና 0-2 ሙገር ሲሚንቶ
መሰሉ አበራ (2)

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-0 እቴጌ
ብሩክታዊት ግርማ (ፍቅም) ፣ ብዙሃን እንዳለ


ረቡዕ ግንቦት 24ቀን 2008

ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ  0-1 ልደታ ክ/ከተማ
ፍፁም ኪሮስ (ፍቅም)

መከላከያ 3-2 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ምስር ኢብራሂም (2) ፣ የምስራች ላቀው | ሄለን ሰይፉ (ፍቅም) ፣ ሜሮን አብዶ


የደረጃ ሰንጠረዥ

PicsArt_1464810449036


የ21ኛ ሳምንት ፕሮግራም

ቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2008

08፡00 ልደታ ክ/ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አአ ስታድየም)

10፡00 ደደቢት ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)

እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2008

08፡00 ሙገር ሲሚንቶ ከ ቅድስት ማርያም ዩኒቨርሰቲ (አአ ስታድየም)

09፡00 ዳሽን ቢራ ከ መከላከያ (ጎንደር)

10፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና (አአ ስታድየም)


ተጨማሪ ዜና | የደቡብ-ምስራቅ ዞን ተጠናቋል


Leave a Reply