የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 19ኛ ሳምንት 12 ጨዋታዎች ዛሬ ሲካሄዱ ከምድብ ሀ በደረጃ ሰንጠረዡ ከ1-5 የሚገኙት ክለቦች ነጥብ ጥለዋል፡፡ በምድብ ለ መሪዎቹን በመከተል ላይ የሚገኙት ክለቦች ወጥ አቋም ማሳየት አልቻሉም፡፡
የምድብ ሀን እየመራ ወደ አዲግራት የተጓዘው ወልድያ 2-1 ተሸንፎ መሪነቱን አስረክቧል፡፡ ፋሲል ከውሃ ስፖርት ካለ ግብአቻ ቢለያይም በግብ ልዩነቶች የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀምሯል፡፡
የሁለቱ ክለቦች ነጥብ መጣል ለተከታዮቹ መልካም አጋጣሚ ቢፈጥርም ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡
ከምድብ ለ በ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ምክንያት ጨዋታ ያላደረጉት ጅማ አባ ቡና እና አአ ከተማን የሚጠጋ ክለብ አልተገኘም፡፡ ሀላባ ከተማ ከጅማ ከተማ ነጥብ ሲጋራ ከወራቤ ከተማ በቀር ተከታዮቹ ክለቦች ድል ማስመዝገብ ተስኗቸዋል፡፡
የሳምንቱ ውጤቶች እና ግብ አግቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
ምድብ ሀ
አማራ ውሃ ስራ 1-1 መቀለ ከተማ
ሰኢድ ሀሰን | ሙሉጌታ ኤዶም
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ 2-1 ወልዲያ
ብሩክ ፣ አብዱልሰላም | በድሩ ከማል
ቡራዩ ከተማ 1-0 ባህርዳር ከተማ
ሙከረም ሀለቶ
ሰበታ ከተማ 3-0 ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን
ሄኖክ ፣ ናትናኤል (ፍቅም) ኤልያስ
ፋሲል ከተማ 0-0 ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት
ኢትዮጵያ መድን 0-0 አክሱም ከተማ
አዲስ አበባ ፖሊስ 0-0 ወሎ ኮምቦልቻ
ምድብ ለ
አርሲ ነገሌ 1-0 ሻሸመኔ ከተማ
አገኘለሁ ልኬሳ
አአ ዩኒቨርሲቲ 0-2 ወራቤ ከተማ
ፀደቀ ግርማ እና አብዱልራዛቅ ናስር
ነገሌ ቦረና 2-1 ድሬዳዋ ፖሊስ
ዳግም በቀለ ፣ አብዲ ሁሴን | ኢብራሂም
ሀላባ ከተማ 1-1 ጅማ ከተማ
አስቻለው ሁታ | ንጋቱ
ባቱ ከተማ 1-2 ጂንካ ከተማ
ሀብታሙ ሻጋ | አቤኔዘር አቶ ፣ አብነት ተሾመ
ናሽናል ሴሜንት 1-1 ነቀምት ከተማ
ሙህዲን ሙሳ | ኢሳ በፍቃዱ
* የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሊጠናቀቅ የ11 ሳምንት እድሜ ሲቀረው ከየምድቦቹ 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡ 4 ክለቦት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያድጋሉ፡፡ ፕሪሚየርሊጉ በቀጣይ የውድድር ዘመን በ16 ክለቦች መካከል ይደረጋል፡፡