ጋቦን 2017: በአምላክ ተሰማ እና ረዳቶቹ የሞሪሽስ እና ጋና ጨዋታን ይመራሉ

የ2017 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ በምድብ 8 ትሪያኖን ላይ ሞሪሸስ ጋናን ታስተናግዳለች፡፡ ይህን ጨዋታም ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንደሚመሩት ካፈ አስታውቋል፡፡

ጨዋታውን በዋና ዳኝነት የሚመራው በአምላክ ተሰማ ሲሆን ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል ረዳት ዳኞች ናቸው፡፡ ኃይለየሱስ ባዘዘው ደግሞ 4ኛ ዳኛ ሆኖ ጨዋታውን ይመራል፡፡

IMG_4101-608x360

ኃይለየሱስ ይህን ጨዋታ ካካሄደ በኀላ ጉዞውን ወደ ግብፅ በማድረግ በቀጣዩ ሳምንት ግብፅ ከ ሩዋንዳ የሚያደርጉትን የአፍሪካ ከ20 አመት ዋንጫ ጨዋታን ይመራል፡፡ የሃይለየሱስ ረዳቶች ተደርገው የተመረጡት ትግል ግዛው እና በላቸው ይታየው ሲሆኑ አርቢቴር በላይ 4ኛ ዳኛ ሆነው ይጓዛሉ፡፡

በተያያዘ ዜና ዛሬ የሚካሄደው የሌሶቶ እና ኢትዮጵያን ጨዋታ የሞሪሸስ ዳኞች እንደሚመሩ ታውቋል፡፡

በዋና ዳኝነት ፓርሜንድራ ኩንዶ ሲመሩ ጄን ቴልቫር እና አክታር ሮሳዬ በረዳትነት ይመራሉ፡፡

Leave a Reply