ሌሶቶ ከ ኢትዮጵያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ሌሶቶ 1-2 ኢትዮጵያ
58′ ጄን ታባ-ኒትሶ | 45+2′ 53′ ጌታነህ ከበደ


ተጠናቀቀ !!!
ጨዋታው በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ ኢትዮጵያ ከ5 ጨዋታ 8 ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ ደረጃዋን አጠናክራለች፡፡

የተጫዋች ለውጥ
90+1′
ሽመክት ጉግሳ ወጥቶ ኤልያስ ማሞ ገብቷል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

85′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች እንቅስቃሴውን ለማረጋጋት በመጣር ላይ ይገኛሉ፡፡

82′ ሲትሮ ማኔ ከግራ መስመር የመታውን ኳስ አቤል ቢተፋውም በፍጥነት ይዞታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
70′
ዳዊት ፍቃዱ ወጥቶ ምንተስኖት አዳነ ገብቷል፡፡

69′ ጌታነህ ከበደ በግራ እግሩ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
67′
አቤል ማሞ ደቂቃ አባክኗል ቀሚል የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ
61′
ሽመልስ በቀለ ወጥቶ አስራት መገርሳ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
59′
አንተነህ ተስፋዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመለክቷል፡፡

ጎልል ሌሶቶ
58′ ሌሶቶዎች ወደ ጨዋታው የመለሰቻቸውን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ጄን ታባ-ኒትሶ ከመስመር የተሻማው ኳስ ሲመለስ በቮሊ ከመረብ አሳርፏል፡፡

53′ ጎልልልል ኢትዮጵያ
ጌታነህ ከበደ በድጋሚ!
የሌሶቶ ተከላካይ ወደ ኀላ ሲመልስ በማጠሩ ምክንያት ያገኘውን ኳስ የግብ ጠባቂው ጆዊስን መውጣት ተመልክቶ በአናቱ መጥኖ በመምታት ከመረብ አሳርፏል፡፡

51′ ከርቀት የተሞከረውን ኳስ አቤል ማሞ በአግባቡ መቆጣጠር አልቻለም፡፡ ሌሶቶዎችበሁለተኛው አጋማሽ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

PicsArt_1465135110893

ጎልልልልልልል!!!!! ጌታነህ ከበደ
45+2′ ጌታነህ ከበደ ከፍጹም ቅጣት ምት ጠርዝ በግሩም ቅልጥፍና አዙሮ የመታው ኳስ ከመረብ አርፏል፡፡ ግሩም ግብ፡፡

45′ መደበኛው የመጀመርያ አጋማሽ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

43′ አብዱልከሪም ከርቀት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ጆዊስ አውጥቶታል፡፡ ጆዊስ ጥሩ ቀን እያሳለፈ ይገኛል፡፡

** የኢትዮጵያ ደጋፊዎች በስታድየሙ ይታያሉ፡፡ ሌሶቶ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መገኘቷ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት እንዲገኙ አድርጓል፡፡

PicsArt_1465135368033

31′ ጌታነህ ከበደ በግቡ የቀኝ መስመር ያገኘውን ኳስ ጆዊስ አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
28′ አስቻለው ታመነ ኳስ በእጁ በመንካቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

27′ ሴቱርማኒ አደገኛ ኳስ ይዞ ለመግባት ሲሞክር አንተነህ ተስፋዬ ሸርታቴ ወርዶ አስጥሎታል፡፡

23′ አብዱልከሪም ከመስመር የመታውን ኳስ ጆዊስ አውጥቶታል፡፡

21′ ጌታነህ ከመስመር ያሻማውን ኳስ የሌሶቶ ተከላካይ አውጥቶታል፡፡

20′ ኢትዮጵያ በፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ ጨዋታውን ብትጀምርም አሁን ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

12′ ሌሶቶዎች ከቅጣት ምት የሞከሩትን ኳስ አቤል ማሞ ይዞታል፡፡

9′ የተሻማውን የማዕዘን ምት ዳዊት ፍቃዱ ሞክሮ የግቡ ቋሚ ለትሞ ተመልሷል፡፡ በተተረማመሰ ሁኔታ ውስጥ ዳዊት በድጋሚ ጥሩ የማግባት ሙከራ አድርጎ ወጥቶበታል፡፡

8′ በረጅሙ የተሻገረውን ኳስ የሌሶቶ ተከላካይ ሲመልሰው ጌታነል መትቶ ግብ ጠባቂው አድኖበታል፡፡

ኢትዮጵያ በፈጣን ቅብብል ወደ ግብ በመድረስ ላይ ትገኛለች፡፡

1′ ሽመልስ ከማዕዘን ምት ይዞ በመምጣት ለጌታነህ ያመቻቸለትን ኳስ ጌታነህ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

1′ ሽመክት ጉግሳ የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው አውጥቶበታል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ አማካኝነት ተጀመረ፡፡


የሌሶቶ አሰላለፍ
ጆሉስ

ሞርሞሆሎ – ማክፔ (አምበል) – ሴካ – ሴሎ

ጀርሚያ ካሜላ – ፖትሎን – ሶኖፖ – ፖል ጄን – ታባ ኒትሶ

ሴፖ ሴትሩማኒ

የኢትዮጵያ አሰላለፍ

1 አቤል ማሞ

2 አብዱልከሪም መሃመድ – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አንተነህ ተስፋዬ – 13 አህመድ ረሺድ

14 ሽመክት ጉግሳ – 6 ጋቶች ፓኖም – 18 ሽመልስ በቀለ – 5 ኤፍሬም አሻሞ

9 ጌታነህ ከበደ (አምበል) – 11 ዳዊት ፍቃዱ


ተጠባባቂዎች
ጀማል ጣሰው
ደስታ ዮሃንስ
ያሬድ ባየህ
ምንተስኖት አዳነ
ኤልያስ ማሞ
አስራት መገርሳ
ታፈሰ ተስፋዬ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *