የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡
ሀዋሳ ላይ የዞኑ ቻምፒዮን መሆኑን ባለፈው ሳምንት ያረጋገጠው ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና አቻ ተለያይቷል፡፡ አዳማ ላይ ደግሞ አዳማ ከተማ ወላይታ ድቻን 3-1 በመርታት በ2ኛ ደረጃነት አጠናቋል፡፡
4 ክለቦች በተሳተፉበት የዘንድሮው የውድድር ዘመን ሀዋሳ በ12 ነጥብ ቻምፒዮን ሲሆን አዳማ በ10 ፣ ሲዳማ ቡና በ7 ፣ ወላይታ ድቻ በ4 ነጥቦች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል፡፡
የ8ኛ ሳምንት ውጤቶች
ሀዋሳ ከተማ 2-2 ሲዳማ ቡና
ወድማገኝ ታደሰ ፣ ፀጋአብ ዮሴ | ፋሲል ሽብሩ ፣ ይገዙ ቦጋለ
አዳማ ከተማ 3-1 ወላይታ ድቻ
የኀላሸት ፍቃዱ (2) ፣ አዲሱ መገርሳ (ፍቅም) | አክሊሉ ዋና (ፍቅም)
ማስታወሻ
– የጥሎ ማለፍ ውድድር ከሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ውድድር ለማድረግ ታስቧል፡፡
– የመካከለኛ ዞን ሊጠናቀቅ 2 ሳምንታት ይቀረዋል፡፡
– የማጠቃለያ ወድድሩ በ10 ክለቦች መካከል ይደረጋል፡፡ ከመካከለኛው 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ 4 ክለቦች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
– ከመካከለኛው ዞን 4 ቡድኖች (ደደቢት ፣ ንግድ ባንክ ፣ ሐረር ሲቲ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ) ለማጠቃለያው ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
– የደቡብ-ምስራቅ ዞን ተሳታፊ የሆኑት ሁሉም ክለቦች ወደ ማጠቃለያ ውድድሩ ያልፋሉ፡፡
– ውድድሩ በአዳማ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡