ለአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ከማሊ ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 5-0 ተሸንፏል፡፡
ሁለቱም ቡድኖች በ90 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ 23 ተጨዋቾቻቸውን በዘጠና የተጠቀሙ ሲሆን የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በመጀመርያው አጋማሽ በጋናው ጨዋታ ላይ ቋሚ ተሰላፊ የነበሩትን ተጠቅሟል፡፡ በዚህ ክፍለ ጊዜም 2-0 እየተመራወደ መልበሻ ክፍል አምርቷል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ የተጫወቱት ቀሪ የቡድን አባላት ሶስት ግቦች አስተናግደው ጨዋታው በማሊ 5-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ ነገ በኛ ሰአት አቆጣጠር 5:45 ላይ ወደ ጋና የሚያቀና ይሆናል፡፡