ደደቢት ከ ዳሽን ቢራ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ደደቢት 4-1 ዳሽን ቢራ
66′ 29′ 90+4′ ዳዊት ፍቃዱ 78′ ሳሙኤል ሳኑሚ | 9′ የተሻ ግዛው


ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በደደቢት አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት
90+4′ ዳዊት ፍቃዱ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ሐት-ትሪክ የሰራበትን ኳስ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ጭማሪ ደቂቃ
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

83′ ያሬድ ባየህ ከርቀት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት
78′ ከሽመክት የተሻገረለትን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ ወደ ግብነት ለውጦታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ዳሽን
75′
ሳሙኤል አለባቸው ወጥቶ ተክሉ ተስፋዬ ገብቷል፡፡

73′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ኤርሚያስ ሃይሉ ሞክሮ ታሪክ አድኖበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ዳሽን ቢራ
67′
ምንያህል ይመር ወጥቶ መሃመድ ሸሪፍ ዲን ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!! ደደቢት
66′ ዳዊት ፍቃዱ ከርቀት የመታው ኳስ በተከላካዮች ተጨርፎ ግብ ሆኗል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
61′
ምኞት ደበበ ወጥቶ ተካልኝ ደጀኔ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
58′
ሳሙኤል አለባቸው የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

56′ ሳኑሚ ያሻገረውን ኳስ ዳዊት ፍቃዱ በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

54′ በአንድ ሁለት ቅብብል የተቀበለውን ኳስ ሳሙኤል አለባቸው ከርቀት ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

51′ ሳኑሚ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ዳዊት ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ተጀመረ!!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ
ኤዶመም ሆሶዎሮቪ ወጥቶ ኤርሚያስ ሃይሉ ገብቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ጭማሪ ደቂቃ
45′
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

40′ ጨዋታው ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግብ መቅረብ አልቻሉም፡፡

ጎልልል!!! ደደቢት
29′ ዳዊት ፍቃዱ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ደደቢትን አቻ አድርጓል፡፡

15′ የተሻ ግዛው የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

13′ ዳዊት ፍቃዱ ከሳጥኑ ጠርዝ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ጎልል!!! ዳሽን ቢራ
9′
የተሻ ግዛው ከመስመር ወደ ውስጥ አጥብቦ በመግባት ዳሽንን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የደደቢት አሰላለፍ

22 ታሪክ ጌትነት

14 አክሊሉ አየነው – 29 ምኞት ደበበ – 5 አይናለም ሃይለ – 10 ብርሃኑ ቦጋለ

19 ሽመክት ጉግሳ – 21 ኄኖክ ካሳሁን – – 8 ሳምሶን ጥላሁን – 7 ስዩም ተስፋዬ

17 ዳዊት ፍቃዱ – ሳሙኤል ሳኑሚ

ተጠባባቂዎች
30 ብርሃኔ ፍስሃዬ
2 ተካልኝ ደጀኔ
15 ጆን ቱፎር
32 ክዌሲኬሊ
27 አለምአንተ ካሳ
6 እንዳለ ከበደ
20 ኤፍሬም ጌታቸው

የዳሽን ቢራ አሰላለፍ

1 ደረጄ አለሙ

23 ዮናስ ግርማይ – 2 አሌክስ ተሰማ – 26 ያሬድ ባየህ – 21 አምሳሉ ጥላሁን

4 አስራት መገርሳ – 5 ሳሙኤል አለባቸው – 8 ምንያህል ይመር

7 መስፍን ኪዳኔ – 9 ኤዶም ሆውሶሮቪ – 10 የተሻ ግዛው

ተጠባባቂዎች
31 ቴዎድሮስ ጌትነት
3 ሱሌማን መሃመድ
17 ብርሃኑ በላይ
25 መሃመድ ሸሪፍ ዲን
30 ተክሉ ተስፋዬ
20 ኦስማን ካማራ
11 ኤርሚያስ ሃይሉ

1 Comment

Leave a Reply