ብሄራዊ ሊግ፡ ደሴ ከተማ እና አንባሪቾ ወደ ማጠቃለያው ውድድር ያለፉ የመጀመርያዎቹ ክለቦች ሆነዋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የዞኖች ውድድር ወደ ማገባደጃው እየተቃረበ ነው፡፡ ደሴ ከተማ እና አንባሪቾም የማጠቃለያ ውድድር ትኬታቸውን የቆረጡ መጀመርያዎቹ ክለቦች ሆነዋል፡፡

በሰሜን-ምዕራብ ዞን ምድብ ለ የሚገኘው ደሴ ከተማ ወደ ማጠቃለያው ማለፉን ለማረጋገጥ 1 ነጥብ በቂው የነበረ ሲሆን እሁድ ባደረገው ጨዋታም ከሰሎዳ አድዋ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው ማለፉን አረጋግጧል፡፡

ከሌሎች ዞኖች ከፍ ያለ ቁጥር ባለው የደቡብ-ምዕራብ ዞን ምድብ ለ የሚገኘው አንባሪቾ ሁለት ጨዋታ እየቀረው ወደ ማጠቃለያው ዙር የሚያሳልፈውን ድል ቡሌ ሆራ ላይ አስመዝግቧል፡፡

በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በየሳምቱ መከሰቱን የቀጠለው የስታድየም ግርግር እና ረብሻ በዚህ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ላይም ተከስተዋል፡፡ ወልቂጤ ከተማ ከ ወሊሶ ከተማ ፣ ዩኒቲ ጋምቤላ ከ መቱ ከተማ እንዲሁም ጋርዱላ ከኮንሶ ኒውዮርክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች የተቋረጡ ሲሆን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኮሚሽነሮቸን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ የሚወስነው ውሳኔ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በ16 ክለበቾ መካከል የሚካሄድ ሲሆን መቼ እና የት እንደሚካሄድ እስካሁን አልታወቀም፡፡ ከየዞኑ 1ኛ እና 2ኛ የሚወጡ ክለቦች በቀጥታ ወደ ማጠቃለያው ሲያልፉ በየዞኑ 3ኛ የወጡት ቡድኖች ነጥባቸው ካደረጉት ጨዋታ ጋር ተሰልቶ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ሁለት ቡድኖች ወደ ማጠቃለያው ያልፋሉ፡፡


የሳምንቱ ውጤቶች እና የደረጃ ሰንጠረዦች ይህንን ይመስላሉ፡-

 ሰሜን-ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ (12ኛ ሳምንት) 

እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

አምባ ጊዮርጊስ 0-1 ዳባት ከተማ

ደባርቅ 1-1 አዊ አምፒልታቅ

ዳሞት ከተማ 1-1 አማራ ፖሊስ

-ጎጃም ደብረማርቆስ በዚህ ሳምንት አራፊ ቡድን ነው

-ሊጠናቀቅ 2 ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465899319023

 ሰሜን-ምዕራብ ዞን ምድብ ለ (7ኛ ሳምንት) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

ደሴ ከተማ 1-1 ሰሎዳ አድዋ

ትግራይ ውሃ ስራ 1-2 ሽረ እንዳስላሴ

ላስታ ላሊበላ 0-2 ዋልታ ፖሊስ

-ሊጠናቀቅ አንድ ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465898829417

 ደቡብ-ምዕራብ ዞን ምድብ ሀ (7ኛ ሳምንት) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

አሶሳ ከተማ 2-0 ጋምቤላ ከተማ

ዩኒቲ ጋምቤላ – መቱ ከተማ (ተቋርጧል)

ሚዛን አማን 1-1 ከፋ ቡና

-ሊጠናቀቅ 1 ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465898753140

 ደቡብ-ምዕራብ ዞን ምድብ ለ (16ኛ ሳምንት) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

ጋርዱላ – ኮንሶ ኒውዮርክ (ተቋርጧል)

ዲላ ከተማ 2-0 ጎባ ከተማ

ሮቤ ከተማ 2-0 ጎፋ ባሪንቾ

አንባሪቾ 2-0 ቡሌ ሆራ

-ወላይታ ሶዶ በዚህ ሳምንት አራፊ ነው

-ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465899263496

 መካከለኛ ዞን ምድብ ሀ (16ኛ ሳምንት) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

ቡታጅራ ከተማ 1-0 ቦሌ ክ/ከተማ

ለገጣፎ 0-0 የካ ክ/ከተማ

ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2008

09፡00 ልደታ ክ/ከተማ ከ ቱሉ ቦሎ (አበበ ቢቂላ)

ረቡዕ ሰኔ 8 ቀን 2008

08፡00 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከ ዱከም ከተማ (አበበ ቢቂላ)

-መቂ ከተማ በዚህ ሳምንት አራፊ ነው፡፡

-ሊጠናቀቅ 2 ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465898988251

 መካከለኛ ዞን ምድብ ለ (13ኛ ሳምንት) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

ጨፌ ዶንሳ 2-0 ሆለታ ከተማ

ወልቂጤ ከተማ – ወሊሶ ከተማ (ተቋርጧል)

ረቡዕ ሰኔ 8 ቀን 2008

06፡00 አዲስ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ክ/ከተማ (አበበ ቢቂላ)

10፡00 ቦሌ ገርጂ ዩኒየን አምቦ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

-ሊጠናቀቅ 1 ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465898908985

 ምስራቅ ዞን (ተስተካካይ ጨዋታ) 
እሁድ ሰኔ 5 ቀን 2008

ካሊ ጅግጅጋ 2-4 ቢሾፍቱ ከተማ

-ሊጠናቀቅ 2 ሳምንት ይቀረዋል

PicsArt_1465898622956

Leave a Reply