ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
72′ ተስፋዬ አለባቸው


ተጠናቀቀ
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የውድድር ዘመኑን በድል ለማጠናቀቅም እጅግ እጅግ ተቃርቧል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
84′
ምንተስኖት አዳነ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል

* የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ቻምፒዮንነትን የሚያበስሩ መዝሙሮችን በመዘመር ላይ ይገኛሉ፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ንግድ ባንክ
81′
አብዱልከሪም ሀሰን ወጥቶ ዳኛቸው በቀለ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
80′
ራምኬል ሎክ ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡

79′ አብዱልከሪም ወደ ጎል የመታው ኳስ በተከላካዮች ተደርቦ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

78′ አዳነ ግርማ ከርቀት በግራ እግሩ የመታውን ኳስ ፌቮ ይዞበታል፡፡

ቀይ ካርድ
75′
ፊሊፕ ዳውዚ ከረዳት ዳኛው ጋር በፈጠረው ውዝግብ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡

ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
72′ ተስፋዬ አለበቸው ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ ፌቮን አልፎ ከመረብ አልፏል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
65′
ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ሳላዲን ሰኢድ ገብቷል፡፡

65′ ፊሊፕ ዳውዚ ከመስመር ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ቢያቀብለውም ምአብዱልከሪም በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡

61′ ራምኬል ሎክ ከመስመር ጠንከር አድርጎ የላከውን ኳስ አዳነ ግርማ ሳይደርስበት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

57′ በሃይሉ አሰፋ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ፌቮ አውጥቶታል፡፡ አሁን ጨዋታው ሞቅ እያለ ሄዷል፡፡

55′ ኤፍሬም አሻሞ የመታውን ኳስ ኦዶንካራ ሲመልሰው አምሃ በለጠ አግኝቶ ወደ ግብ ቢሞክርም ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡

46′ ምንያህል ተሾመ ከረጅም ርቀት የሞከረውን ኳስ ፌቮ አውጥቶታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት የተጫዋች ለውጥ
ቢንያም በላይ ወጥቶ አምሃ በለጠ ገብቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የመጀመርያ አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

41′ ምንተስኖት አዳነ ከሳጥን ውስጥ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

40′ ጨዋታው እጅግ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ባለፉት 15 ደቂቃዎችም የረባ እንቅስቃሴ መመልከት አልቻልንም፡፡

ቢጫ ካርድ
25′
ጋብሬል አህመድ ኳስ በእጅ በመንካቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

24′ ፊሊፕ ዳውዚ ከርቀት የመታውን ኳስ ኦዶንካራ መቆጣጠር ባለመቻሉ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

20′ በሃይሉ አሰፋ ወደ ውስጥ አጥብቦ በመግባት የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

15′ የመጀመርያዎቹን 10 ደቂቃዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ጫና ፈጥሮ ሲንቀሳቀስ ያለፉት 5 ደቂቃዎች በመሃል ሜዳ ያመዘነ እንቅስቃሴ ታይቷል፡፡

7′ ከራምኬል ሎክ ያሻገረውን ኳስ በሃይሉ በቮሊ ቢሞክረውም አቅጣጫውን ቀይሮ ወጥቷል፡፡

2′ ተስፋዬ አለባቸው ከርቀት የመታውን ኳስ ፌቮ አውጥቶታል፡፡ በሃይሉ ያሻማውን የማዕዘን ምት አስቻለው በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
1 ኢማኑኤል ፌቮ

15 አዲሱ ሰይፉ – 16 ቢንያም ሲራጅ – 5 ቶክ ጀምስ – 27 አንተነህ ገብረክርስቶስ

4 ጋብሬል አህመድ

21 ኤፍሬም አሻሞ – 80 ቢንያም በላይ – 11 አብዱልከሪም ሀሰን – 2 ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን

9 ፊሊፕ ዳውዚ


ተጠባባቂዎች
64 ዳዊት አሰፋ
98 ዳንኤል አድሃኖም
12 አቤል አበበ
6 አምሃ በለጠ
8 ሰለሞን ገብረመድህን
18 ታድዮስ ወልዴ
10 ዳኛቸው በቀለ


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 2 መሃሪ መና

9 ምንያህል ተሾመ – 21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ

17 ራምኬል ሎክ – 19 አዳነ ግርማ – 7 በሃይሉ አሰፋ


ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
14 አለማየሁ ሙለታ
4 አበባው ቡታቆ
20 ዘካርያስ ቱጂ
26 ናትናኤል ዘለቀ
16 ጎድዊን ቺካ
10 ሳላዲን ሰኢድ


1 Comment

Leave a Reply