አፍሪካ፡ ኤቷል ደ ሳህል በኮንፌዴሬሽን ካፕ መክፈቻ በካውካብ ማራካሽ ተሸንፏል

የቱኒዚያውን ሻምፒዮን በሜዳው ያስተናገደው የሞሮኮው ካውካብ ማራካሽ 2-1 በማሸነፍ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡ ሁለቱም ክለቦች የሰሜን አፍሪካ መሆናቸው ጨዋታውን ጉሽሚያ እንዲኖረው አድርገውታል፡፡

በ61ኛው ደቂቃ በብራዚላዊው ዲያጎ አካስታ ላይ በተሰራው ጥፋት የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት ሃምዛ ላማር ወደ ግብነት ቀይሮ የሶሱን ክለብ ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ኤቷል በሁለት ደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ተጫዋቾችን ማጣታቸው በጨዋታው  ልዩነት እንዲፈጠር አስችሏል፡፡ ጋሃዚ አብዱልራዛክ በ65ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ እንዲሁም ኢሃብ ሳክኒ በ67ኛው ደቂቃ በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግደዋል፡፡ የቁጥር ብልጫ የነበራቸው ካውካቦች በኮያቴ እና አቡበከር አሚሚ ግቦች 2-1 አሸነፈው ወጥተዋል፡፡

 

የዓርብ ውጤት

ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) 2-1 ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

 

ዕሁድ ሰኔ 12/2008

15፡30 – ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ ሚዲአማ (ጋና) (ስታደ ቲፒ ማዜምቤ)

22፡00 – ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) ከ አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) (ኮምፕሌክ ስፖርቲፍ ሞላይ አል ሃሰን)

22፡15 – ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) ከ ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) (ዩናይት መግሪቢን)

 

Leave a Reply