አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዳማ ከተማ 3-1 ወላይታ ድቻ
43′ ሚካኤል ጆርጅ 50′ ሙባረክ ሽኩር (በራሱ ግብ ላይ) 71′ ታፈሰ ተስፋዬ | 75′ አላዛር ፋሲካ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በአዳማ ከተማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
87′
ጃኮብ ፔንዛ ወጥቶ ጃፈር ደሊል ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
79′
ሱራፌል ዳኛቸው ወጥቶ ደሳለኝ ደባሽ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! ወላይታ ድቻ
የድቻ ተጫዋቾች አንድ ሁለት ተቀባብለው በመግባት የአዳማ ተከላካዮች ከጨዋታ ውጪ ብለው በተዘናጉበት አጋጣሚ አላዛር ፋሲካ ግብ አስቆጥሯል፡፡

74′ በቡድናቸው ውጤትና አጨዋወት ተስፋ የቆረጡ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ሜዳውን ለቀው እየወጡ ነው፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
72′
ዮናታን ከበደ ወጥቶ ሻኪሩ ኦላዴ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!! አዳማ ከተማ
71′ ሚካኤል ጆርጅ ያመቻቸለትን ጣጣውን የጨረሰ ኳስ ታፈሰ ተስፋዬ ከመረብ አሳርፎታል፡፡

65′ ታፈሰ ተስፈዬ ከወንድወሰን ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም አልተጠቀመበትም፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

60′ ድቻዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

55′ ፈቱዲን ጀማል የሞከረውን ኳስ ጃኮብ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

ቢጫ ካርድ
54′
ዳኛ ፊሽካ ከነፋ በኃላ ኳሱ አላግባብ በመያዙ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!! አዳማ ከተማ
50′ ሱራፌል በቀኝ መስመር አታሎ በመግባት መሬት ለመሬት ያሻገረውን ኳስ ሙባረክ ሽኩር ለማውጣት ሲሞክር በራሱ ጎል ላይ አስቆጥሯል፡፡ 2-0

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ድቻ
ስንታየሁ መንግስቱ እና በድሉ መርዕድ ወጥተው ሃይለየሱስ ብርሃኑ እና እንዳለ መለዮ ገብተዋል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአዳማ ከተማ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ጎልልል!!! አዳማ ከተማ
43′ ዮናታን ከግራ መስመር ያሻገረውን ኳስ ሚካኤል ጆርጅ በግንባሩ በመግጨት ግሩም ጎል አስቆጥሯል፡፡

36′ ሞገስ ከግብ ጠባቂው ወንድወሰን አንድ ለአንድ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ አግኝቶ ሳይጠቀም ቀርቷል፡፡

30′ አዳማ በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ ቢወስድም ጠጣር የሆነውን የድቻ የተከላካይ ክፍል ሰብሮ ለመግባት ተቸግሯል

22′ ብሩክ ቃልቦሬ ከ16:50 ውጭ አክርሮ የመታው ለጥቂት በግቡ አግዳሚ በላይ አለፋለች፡፡ ጥሩ ሙከራ ነበር

15′ በመጀመርያዎቹ አስር ደቂቃ ከነበረው ፈጣን እንቅስቃሴ ቀዝቀዝ ያለ ጨዋታ እየተመለከትን ነው፡፡ ደጋፊዎቹም በዝምታ ተውጠዋል፡፡

የመጀመርያ ሙከራ!
7′
ሱራፌል ዳኛቸው ከርቀት የመታው ኳስ ወደ ውጭ ወጥቷል፡፡

5′ የጨዋታው የመጀመርያ ደቂቃዎች ፈጣን እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በአዳማ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የአዳማ ከተማ አሰላለፍ

1 ጃኮብ ፔንዛ

20 ሞገስ ታደሰ – 12 ምንተስኖት ከበደ – 5 ተስፋዬ በቀለ

7 ታከለ አለማየሁ – 8 ብሩክ ቃለቦሬ – 19 ፋሲካ አስፋው – 80 ሱራፌል ዳኛቸው – 16 ዮናታን ከበደ

9 ሚካኤል ጆርጅ – 21 ታፈሰ ተስፋዬ

ተጠባባቂዎች
29 ጃፋር ደሊል
3 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ
6 እሸቱ መና
22 ደሳለኝ ደባሽ
15 ጫላ ድሪባ
18 ሻኪሩ ኦላዴ
13 ቢንያም አየለ


የወላይታ ድቻ አሰላለፍ

76 ወንደሰን አሸናፊ

9 ያሬድ ዳዊት – 3 ቶማስ ስምረቱ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 2 ፈቱዲን ጀማል

26 ወንድማገኝ በለጠ – 8 አማኑኤል ተሾመ – 18 በድሉ መርዕድ – 17 በዛብህ መለዮ

20 ስንታየሁ መንግስቱ – 19 አላዛር ፋሲካ

ተጠባባቂዎች
1 መክብብ ደገፉ
5 ዳግም ንጉሴ
21 መሳይ አንጪሶ
12 ፀጋ አለማየሁ
16 ሃይለየሱስ ብርሃኑ
10 እንዳለ መለዮ
23 ጸጋዬ ብርሃኑ

1 Comment

Leave a Reply