የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬም ቀጥሎ ሲውል ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል፡፡ መከላከያ እና ባንክ ደግሞ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡
09:00 ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ደደቢት 1-0 ተሸንፏል፡፡ በጣለው ዝናብ ምክንያት ሜዳው ውሃ በመያዙ ኳስ እንደልብ ማንሸራሸር ባልተቻለበት ጨዋታ ጥቂት የግብ ሙከራዎች ተስተናግደዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ አንዱአለም ንጉሴ በጥሩ ሁኔታ ያመቻቸለትን ኳስ ተጠቅሞ በረከት አዲሱ የሲዳማ ቡናን የድል ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
11:30 ላይ የተገናኙት መከላከያ እና ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡
ግብ በማስቆጠር ቅድሚያውን የያዙት ንግድ ባንኮች ሲሆኑ የፊሊፕ ዳውዚን መቀጣት ተከትሎ የመጀመርያ አሰላለፍ ውስጥ የተካተተው ዳኛቸው በቀለ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሯል፡፡
ከግቡ መቆጠር በኋላ የተሻለ መንቀሳቀስ የቻሉት መከላከያዎች በሳሙኤል ታዬ አማካኝነት አቻ ሆነዋል፡፡ ከግብ ክልሉ የወጣው ፌቮ ኳሱን በአግባቡ ባለማራቁ ያገኘውን ኳስ ሳሙኤል በቀጥታ መትቶ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሁለተኛው አጋማሽ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ የታየበት ሲሆን ይህ ነው የሚባል የግብ ሙከራ ሳይታይ ጨዋታው 1-1 ተጠናቋል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዥ
ከፍተኛ ግብ አግቢዎች
ቀጣይ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታዎች
ሰኞ ሰኔ 13 ቀን 2008
09፡00 አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ (አርባምንጭ)
09:00 ኤሌክትሪክ ከ ሀዲያ ሆሳዕና (አአ ስታድየም)
10፡00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ድሬዳዋ ከተማ (አበበ ቢቂላ-ዝግ ስታድየም)
11፡30 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ዳሽን ቢራ (አአ ስታድየም)