U-17 ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት የመካከለኛ ዞን ቻምፒዮን ሆነ

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት እና ዛሬ ሲደረጉ ደደቢት የዞኑ ቻምፒዮን የሆነበትን ድል አስመዝግቧል፡፡

ዛሬ 03፡00 በአዲስ አበባ ስታዲየም የተገናኙት ደደቢት እና መከላከያ ድንቅ የጨዋታ ፉክክር አድርገው በደደቢት አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጨዋታው በተጀመረ ገና በ10ኛው ደቂቃ  መከላከያዎች በእስጢፋኖስ ዮሃንስ አማካኝነት ጎል አስቆጥረው የመጀመሪያውን አጋማሽ በመሪነት ማጠናቀቅ ችሎ ነበር፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ 56ኛ ደቂቃ ላይ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ የመከላከያ ተጨዋቾች ኳሷን ለማውጣት ባደረጉት ጥረት ሳይሳካላቸው በራሳቸው መረብ ላይ አስቆጥረው አቻ ሲሆኑ መከላከያዎች በዮሃንስ ደረጄ ድንቅ ግብ መሪነቱን በድጋሚ ማግኘት ችለው ነበር፡፡  የኃላ ኃላ ግን መሪነታቸውን ማስጠበቅ ሳይችሉ በዮናስ ብርሃኑ እና በዳንኤል ጌድዮን የ70ኛ እና 84ኛው ደቂቃ ጎሎች 3-2 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ደደቢት 40 ነጥቦች በመሰብሰብ የዞኑ አሸናፊ ሆኗል፡፡


ውጤቶች

ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2008

አፍሮ ፅዮን 1-2 ኢትዮጵያ ቡና

እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2008

ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ 1-5 ሐረር ሲቲ

መከላከያ 2-3 ደደቢት

አዲስ አበባ ከተማ 0-1 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2008

10፡00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ኤሌክትሪክ ሜዳ ፣ ጎፋ)


PicsArt_1466362465254

የማጠቃለያ ውድድር

-10 ክለቦች ይሳተፉበታል

-ከመካከለኛ ዞን 6 ፣ ከደቡብ-ምስራቅ ዞን 4 ክለቦች ይሳተፋሉ፡፡

-በአዳማ አስተናጋጅነት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል


ተሳታፊ ክለቦች

መካከለኛ ዞን ፡ ደደቢት ፣ ሐረር ሲቲ ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መከላከያ ፣ አዲስ አበባ ከተማ

ደቡብ-ምስራቅ ዞን ፡ ሀዋሳ ከተማ (ቻምፒዮን) ፣ ሲዳማ ቡና ፣ አዳማ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *