የጎ-ቴዲ ፉትሳል ዋንጫ መረጃዎች

የ2008 ዓ.ም የጎ-ቴዲ ስፖርት የፉትሳል ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች መከናወናቸውን ቀጥለዋል፡፡

ትላንት ከ7፡00 ሰዓት ጀምሮ በተከናወኑ 4 ጨዋታዎች በአጠቃላይ 50 ጎሎች ሲቆጠሩ ከተከናወኑት ጨዋታዎች በመሸናነፍ የተጠናቀቁት ሁለቱ ብቻ ናቸው፡፡

ብሉቤል ኮምፒዩተር ከኢኤስኤፍ  ባደረጉት የመጀመሪያ የእለቱ ጨዋታ በኢኤስኤፍ 11ለ9 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ በመቀጠል የተከናወነው ጨዋታ ደግሞ ጂኬ ኢትዮጵያ አሴጋን 7ለ2 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል፡፡

ድንቅ የጨዋታ ፉክክር በታየበት ጨዋታ አበበ ቢቂላ ከኪምብሪያ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 8ለ8 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የእለቱ የመጨረሻ መርሃ ግብር በሆነው የትላንት የ10፡00 ሰዓት ጨዋታ ሊና ሆቴልን እና ቲጂ እና ጓደኞቹ ጨዋታ 7ለ7 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

 

ምድብ ሀ

1. ቲጂ እና ጓደኞቹ 3 – 7 – 5

2. ሊና ሆቴል 3 – 1 – 5

3. ኪምብሪያ ኢትዮጵያ 3 – 0 – 3

4. አበበ ቢቂላ 3 – (-8) 1

 

ምድብ ለ

1. ኢትዮጵያን ሶከር ፋውንዴሽን 2 – 12 – 6

2. ጂኬ ኢትዮጵያ 2 – 7 – 6

3. ብሉቤል 2 – (-4) 0

4. አሴጋ ፉትሳል 2 – (-15) 0

 

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን ቢንያም አሰፋ ከኢኤስኤፍ በ17 ጎሎች ሲመራ ለሚ ኢታና ከቲጂና ጓደኞቹ በ10 ጎል ሁለተኛ ነው፡፡ መሃመድ ወርቁ ከቲጂና ጓደኞቹ በ6 ግቦች ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታዎች ረቡዕ ሰኔ15 ሲደረጉ በ03፡00 ኢኤስኤፍ ከ ጂኬ ኢትዮጵያ በ04፡00 ብሉቤል ኮምፒውተር ከአሴጋ ጋር ይጫወታሉ፡፡

Leave a Reply