አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አርባምንጭ ከተማ 2-0 ሀዋሳ ከተማ
8′ ጸጋዬ አበራ 90+5′ ታደለ መንገሻ


ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በአርባምንጭ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል!!! አርባምንጭ
90+5′ ታደለ መንገሻ የአርባምንጭ ከተማን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ያደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

90+2′ በረከት ይስሃቅ በጥሩ እንቅስቃሴ ገብቶ ጥሩ የማግባት አጋጣሚ ቢፈጥርም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
90′
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 5 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

84′ አዲስአለም ተስፋዬ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
74′
እንዳለ ከበደ ወጥቶ ትርታዬ ደመቀ ገብቷል፡፡

70′ መድሀኔ ታደሰ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ አገባው ሲባል አመከነው፡፡

ቢጫ ካርድ
64′
በረከት ወልደጻድቅ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

62′ ጨዋታው በተደጋጋሚ በሚሰሩ ፋውሎች ምክንያት እየተቆራረጠ ይገኛል፡፡

ቢጫ ካርድ
59′
ቢያድግልኝ ኤልያስ ጋዲሳ ላይ በሰራው አደገኛ ፈውል ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡

52′ ጨዋታው ሀይል በተቀላቀለበት እንቅስቃሴ ታጅቦ ቀጥሏል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመሪያው አጋማሽ በአርባምንጭ መሪነት ተጠናቋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
44′ ብርያን ቴቤጎ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ዮሐንስ በዛብህ ገብቷል፡፡ የቴቤጎ ጉዳት ከበድ ያለ በመሆኑ በአምቡላስ ወደ ህክምና ጣቢያ በፍጥነት እየተወሰደ ነው፡፡

41′ በርካታ ቁጥር ያለው ደጋፊ በስታድየም ቢገኝም በዝምታ ተውጦ ጨዋታውን መከታተሉ አስገራሚ ነው፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
35′
ፍርድአወቅ ሲሳይ ወጥቶ መዳህኔ ታደሰ ገብቷል፡፡

26′ ጋዲሳ ቺፕ ያደረገው ኳስ ገባ ተብሎ ሲጠበቅቢያድግልኝ እንደምንም ደርሶ በግንባሩ አወጣው፡፡

23′ ጨዋታው እየተቀዛቀዘ ሲመጣ ይህ ነው የሚባል የተሳካ ቅብብል በሁለቱም በኩል ማየት አልቻልንም፡፡

11′ ከ17 ሜትር የተገኘውን ቅጣት ምት ቢያድግልኝ መቶት ለጥቂት ወጣበት፡፡ አርባምንጭ ጫና ፈጥሮ እየተጫወተ ነው፡፡

ጎልልል!!! አርባምንጭ
8′ ከማዕዘን የተሻገረውን ቴቤጎ ሲያወጣው በቅርብ ርቀት የነበረው ፀጋዬ አበራ አግኝቶ አስቆጥሮታል፡፡

4′ የሀዋሳው ግብ ጠባቂ ቴቤጎ ከበረከት ጋር ተጋጭቶ የህክምና ድጋፍ እያገኘ ነው፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በአርባምንጭ አማካኝነት ተጀመረ::


የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

1 አንተነህ መሳ

2 ወርቅይታደል አበበ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 4 አበበ ጥላሁን – 13 ጸጋዬ አበራ

7 እንዳለ ከበደ – 18 አማኑኤል ጎበና – 21 ምንተስኖት አበራ – 17 ታደለ መንገሻ

9 በረከት ወልደፃዲቅ – 23 ተሾመ ታደሰ

ተጠባባቂዎች
60 መሳይ አያኖ
8 ትርታዬ ደመቀ
3 ታገል አበበ
16 በረከት ቦጋለ
10 መልካሙ ፉንዱሬ
6 ታሪኩ ጎጀሌ
20 አብይ በየነ


የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
18 ብርያን ቴቤጎ

2 ግሩም አሰፋ – 8 ግርማ በቀለ – 6 አዲስአለም ተሰፋዬ – 18 ተስፋ ኤልያስ

3 ኤፍሬም ዘካርያስ – 21ሙሉጌታ ምህረት (አምበል)
13 አስቻለው ግርማ – 5 ታፈሰ ሰሎሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

27 ፍርዳወቅ ሲሳይ

ተጠባባቂዎች
1 ዮሃንስ በዛብህ
22 መላኩ ወልዴ
19 ዮሐንስ ሰገቦ
9 አንተነህ ተሻገር
4 አስጨናቂ ሉቃስ
10 በረከት ይስሃቅ
15 መድሃኔ ታደሰ

2 Comments

Leave a Reply