ቅዱስ ጊዮርጊስ ቻምፒዮንነቱን ሲያረጋግጥ አርባምንጭ ከወራጅ ቀጠናው ያራቀውን ድል አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ኛ ሳምንት ዛሬ በተካሄዱ ጨዋታዎች ተገባዷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቻምፒዮንነቱን ሲያረጋግጥ አርባምንጭ ከወራጅ ቀጠናው ያራቀውን ድል አስመዝግቧል፡፡

ሀዋሳ ከተማን ያስተናገደው አርባምንጭ ከተማ 2-0 በማሸነፍ ላለመውረድ የሚያደርገው ጥረት ላይ ወሳኝ ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
የአርባምንጭ ከተማን የድል ግቦች በመጀመርያዎቹ እና መጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ከመረብ ያሳረፉት ጸጋዬ አበራ እና ታደለ መንገሻ ናቸው፡፡
ድሉን ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ 29 ነጥቦችን በመሰብሰብ 24 ነጥብ ከሰበሰበው ዳሽን ቢራ በ5 ነጥቦች በመራቅ ላለመውረድ የሚያደረገውን ጉዞ አሳምሯል፡፡
PicsArt_1466448252,993

ኤሌክትሪክ መውረዱን ካረጋገጠው ሃዲያ ሆሳዕና ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቶ ላለመውረድ በሚደረገው ትግል ወሳኝ ነጥቦችን ጥሏል፡፡ ግብ በማስቆጠሩ ቅድሚያውን የወሰዱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ሲሆኑ አድናን ቃሲም በቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡ ኤሌክትሪክ በፒተር ኑዋዲኬ አማካኝነት ግብ አስቆጥሮ በአቻ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል ሲያመሩ ከእረፍት መልስ ተምገን ገብረጻድቅ ሀዲያን በድጋሚ መሪ ያደረገች ግብ አስቆጥሯል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃዎች ሲቀሩ ፍፁም ገብረማርያም ኤሌክትሪክን ከሽንፈት የታደገች ግብ ከመረብ አሳርፎ ጨዋታው 2-2 ተፈፅሟል፡፡
ውጤቱ ኤሌክትሪክ ከወራጅ ቀጠናው በ2 ነጥብ ብቻ ርቆ እንዲቀመጥ አስገድዶታል፡፡ የዳሽን ሽንፈትን ተከትሎም ሀዲያ ሆሳዕናን ተከትሎ ላለመውረድ የሚደረገው ትግል በዳሽን ቢራ እና ኤሌክትሪክ መካከል ሆኗል፡፡
PicsArt_1466448123153

አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ በዝግ ስታድየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 3-1 አሸንፏል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በኢኮ ፊቨር ጎል ሲመራ ፍቃዱ ታደሰ ድሬዳዋ ከተማን አቻ አድርጎ የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ ሲካሄድበት ቆይታ ጨዋታው በአቻ ውጤት ይጠናቀቃል ሲባል በጭማሪ ደቂቃዎች አክሊሉ ዋለልኝ እና አማኑኤል ዮሃንስ አስቆጥረው ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
PicsArt_1466448183236

11፡30 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዳሽን ቢራን አስተናገዶ 2-1 በመርታት የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን መሆኑን 2 ጨዋታዎች እየቀሩ አረጋግጧል፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን ሳላዲን ሰኢድ እና አዳነ ግርማ ሲያስቆጥሩ ተቀይሮ የገባው ኤዶም ሆሶውሮቪ ዳሽን ቢራን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ድሉ 51 ነጥቦ የሰበሰበው ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሊጉ ቻምፒዮንነት አብቅቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ድሉ የሊግ ውድድር በኢትዮጵያ ከተጀመረበት 1936 አንስቶ ለ27ኛ ጊዜ በአዲስ መልክ ከተዋቀረበት 1990 በኋላ ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ ቻምፒዮን ሆኗል፡፡
PicsArt_1466448052127

የደረጃ ሰንጠረዥ
PicsArt_1466443871226

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
PicsArt_1466447901586

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *