መከላከያ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

መከላከያ 1-1 ቅዱስ ጊዮርጊስ
9′ መሃመድ ናስር | 90+4′ ዳዋ ሁቴሳ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ መከላከያዎች ከተጨመረው ደቂቃ በላይ አጫውቷል በሚል ከእለቱ ዳኞች ጋር ውዝግብ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! ቅዱስ ጊዮርጊስ
90+4′ ዳዋ ሁቴሳ ከመስመር ወደ ውስጥ በመግባት ግሩም ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

90′ ከመስመር የተሻማው ኳስ ሲመለስ ተስፋዬ አለባቸው አግኝቶ በቀጥታ ቢመታውም ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ጊዮርጊሶች ተደጋጋሚ ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ፡፡

89′ በሃይሉ አሰፋ ከግቡ በቅርብ ርቀት ግልጽ የማግባት አጋጣሚ አግኝቶ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

87′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ዳዋ በጭንቅላቱ በመግጨት ሞክሮ ጀማል በሚገርም ሁኔታ አውጥቶታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
86′ ፍሬው ሰለሞን ወጥቶ በሃይሉ ግርማ ገብቷል፡፡

86′ ዳዋ ከመስመር ወደ ውስጥ በመግባት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – መከላከያ
78′ መሃመድ ናስር ወጥቶ ሳሙኤል ሳሊሶ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
75′ ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡

75′ ተስፋዬ አለባቸው በግምት ከ19 ሜትር የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
68′ ራምኬል ሎክ ወጥቶ በሃይሉ አሰፋ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
64′ ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ ተስፋዬ አለባቸው ገብቷል፡፡

52′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ምንተስኖት በቮሊ ሞክሮ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በመከላከያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45+1′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ሳላዲን በግንባሩ ገጭቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

42′ ከማዕዘን የተሻገረውን ኳስ ሳላዲን በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ቴዎድሮስ በቀለ ከመስመር ላይ አውጥቶታል፡፡

41′ ሳላዲን ሰኢድ መሬት ለመሬት የመታውን ቅጣት ምት ጀማል አውጥቶታል፡፡

ቢጫ ካርድ
41′ መሃመድ ናስር የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

35′ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ መከላከያ የግብ ክልል መጠጋት ቢችልም የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለም፡፡

25′ ሚካኤል ደስታ ከርቀት ቢሞክርም ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
23′
ናትናኤል ዘለቀ በባዬ ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

22′ ናትናኤል ዘለቀ ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

20′ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግብ ከመድረስ ተቆጥበው እንቅስቃሴያቸውን መሃል ሜዳ ላይ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ጎልልል!!! መከላከያ
9′ መሃመድ ናስር የሮበርት ኦዶንካራን ስህተት ተጠቅሞ መከላከያን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

ተጀመረ!!!
ጨዋታው በመከላከያ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

** የመከላከያ ተጫዋቾች በሰልፍ እያጨበጨቡ ሻምፒዮኖቹ ቅዱስ ጊዮርጊሶችን ወደ ሜዳ አስገብተዋል፡፡


የመከላከያ አሰላለፍ

1 ጀማል ጣሰው

2 ሽመልስ ተገኝ – 16 አዲሱ ተስፋዬ – 3 ቴዎድሮስ በቀለ – 6 ታፈሰ ሰርካ

10 ፍሬው ሰለሞን – 26 ኡጉታ ኦዶክ – 13 ሚካኤል ደስታ – 19 ሳሙኤል ታዬ

12 ባዬ ገዛኸኝ – 17 መሃመድ ናስር

ተጠባባቂዎች
22 ይድነቃቸው ኪዳኔ
7 ማራኪ ወርቁ
18 ሙጃኢድ መሃመድ
29 ሙሉቀን ደሳለኝ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ
21 በሃይሉ ግርማ
20 ካርሎስ ዳምጠው


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 3 መሃሪ መና

26 ናትናኤል ዘለቀ – 23 ምንተስኖት አዳነ

17 ራምኬል ሎክ – 19 አዳነ ግርማ – 9 ምንያህል ተሾመ

10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
4 አበባው ቡታቆ
7 በሃይሉ አሰፋ
20 ዳዋ ሁቴሳ
2 ፍሬዘር ካሳ
20 ዘካሪያስ ቱጂ
21 ተስፋዬ አለባቸው

2 Comments

  1. Betam yamiral! enameseginalen!!!!!
    yekefitegna legue bichemerbet?

Leave a Reply