ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፡ የምድብ ለ ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቶታል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በሀዋሳ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡ የምድብ ሁለት ጨዋታዎችም ዛሬ ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ 1-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የድሬዳዋን ድንቅነሽ በቀለ ስታስቆጥር ለኤሌክትሪክ አይናለም ፀጋዬ ከመረብ አሳርፋለች፡፡

ሀዋሳ ከተማ አስቀድሞ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፉን ያረጋገጠው ዳሽን ቢራን 2-1 አሸንፏል፡፡ የሀዋሳን ሁለት የድል ግቦች ምርቃት ፈለቀ ከመረብ ስታሳርፍ ሄለን እሸቱ የዳሽንን ግብ አስቆጥራለች፡፡

ከዚህ ምድብ ሁሉንም ጨዋታዎች በድል የተወጣው ንግድ ባንክ እና 6 ነጥቦች የሰበሰበው ዳሽን ቢራ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ሲያልፉ ከደቡብ-ምስራቅ የተወከሉት ሀዋሳ ከተማ እና ድሬዳዋ ሳይቀናቸው ቀርቷል፡፡ በተለይም የዞኑ ቻምፒዮን የነበረውና ውድድሩን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተጠበቀው በታች ውጤት አስመዝግቧል፡፡

PicsArt_1466966659701

የማጠቃለያ ውድድሩ ነገ ሲቀጥል የምድብ አንድ የመጨረሻ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በ08:00 ወደ ግማሽ ፍፃሜው መግባቱን ያረጋገጠው ደደቢት ቅዱስ ጊዮርጊስን ይገጥማል፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ይህ ጨዋታ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ለማለፍ በማሸነፍ ላይ ብቻ የተመሰረተ በመሆኑ ወሳኝ ነው፡፡ 10:00 ላይ መውደቃቸውን ያረጋገጡት አርባምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ይጫወታሉ፡፡

PicsArt_1466874383394

የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን የደደቢቷ ሎዛ አበራ በ6 ስትመራ የንግድ ባንኳ ሽታዬ ሲሳይ በ5 ትከተላለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *