በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 20ኛ ሳምንት ወልድያ መልካ ቆሌ ስታድየም ላይ ሰኔ 4 ቀን 2008 በወልድያ እና አማራ ውሃ ስራ መካከል ሲደረግ የነበረው ጨዋታ በእረፍት ሰአት መቋረጡ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ እና የውድድር እና ስነስርአት ኮሚቴ ከትላንት በስቲያ ባደረጉት ስብሰባ ጥፋተኛ በተባሉት ላይ ቅጣት ለመጣል ከውሳኔ ተደርሷል፡፡
በውሳኔው መሰረት ወልድያ 3 ነጥብ እና 3 ንፁህ ግብ እንዲያገኝ የተወሰነለት ሲሆን አማራ ውሃ ስራ የኮሚሽነር ውሳኔን ባለማክበር እንዲሁም የተገኘውን ተመልካች ባለማክርና እና በሌሎች የዲሲፕሊን ጥሰቶች ምክንያት ፎርፌ እንዲሰጥበት እንዲሁም 15000 ብር እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡
ውሳኔውን ተከትሎ ወልድያ 47 ነጥብ በመያዝ መሪነቱን ከፋሲል ከተማ ተረክቧል፡፡
የውሳኔውን ሙሉ ዝርዝር ከፌዴሬሽኑ እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡