አፍሪካ፡ የኮንፌድሬሽን ካፕ ሁለተኛ የምድብ መርሃ ግብር ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ

የ2016 ኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ሲጀምሩ ብቸኛው የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ያንግ አፍሪካንስ በውድድር ዓመቱ በካፍ የክለቦች ጨዋታ ላይ ከሜዳው ውጪ ማሸነፍ የተሳነውን ቲፒ ማዜምቤን ያስተናግዳል፡፡ አል አሃሊ ትሪፖሊ ቱኒዚያ ላይ በገለልተኛ ሜዳ ካውካብ ማራካሽን ይገጥማል፡፡

በቱርክ ከነበረው ጠንካራ ዝግጅት በኃላ በኤምኦ ቤጃያ የተሸነፈው ያንግ አፍሪካንስ የምድብ አንድ መሪ ቲፒ ማዜምቤን ዳሬ ሰላም ላይ ይገጥማል፡፡ ማዜምቤ በምድብ መክፈቻ ጨዋታ ሚዲአማን 3-1 የረታ ሲሆን በውድድር ዓመቱ በካፍ ውድድሮች ላይ ከሜዳው ውጪ ያለው መጥፎ ሪከርድ ለማሻሻል ወደ ሜዳ ይገባል፡፡

ሜዳ ላይ ካለ ነገር  ይልቅ የማዜምቤ ክለብ ባለቤት የሆኑት ሞይስ ካቱምቢ በሌሉበት በእስር እንዲቀጡ የሉቡምባሺ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን አግኝቷል፡፡

ዛምቢያዊው የመሃል ሜዳ ተጫዋች ሬንፎርድ ካላባ በድንቅ ብቃቱ ላይ መገኘቱ ማዜምቤዎች ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓል፡፡ ያንጋ በሜዳው ለማሸነፍ አዳጋች ክለብ ሲሆን ቲፒ ማዜምቤን የመርታት አቅም አለው፡፡

የያንጋ ተቀናቃኝ ክለብ የሆነው የሲምባ ደጋፊዎች ከወዲሁ ለቲፒ ማዜምቤ ድጋፋቸውን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል፡፡ በ2014 የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ እንዲሁ 20ሺህ የሚጠጉ የሲምባ ደጋፊዎች ያንጋ ከአል አሃሊ ሲጫወቱ ለግብፁ ክለብ ድጋፋቸውን ለመስጠት ወደ ሜዳ ገብተው ነበር፡፡

በምድብ ሁለት የሰሜን አፍሪካ ደርቢ ቱኒዚያ ላይ በአል አሃሊ ትሪፖሊ እና ካውካብ ማራካሽ መካከል ይደረጋል፡፡ ካውካብ ማራካሽ በምድብ መክፈቻ ጨዋታ ኤቷል ደ ሳህልን ያሸነፈ ሲሆን አሃሊ ትሪፖሊ በፉስ ራባት በጠባብ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ካውካብ ማራካሽ ወደ ግማሽ ፍፃሜው የሚወስደውን መንገድ ለማመቻቸት እንዲሁም አሃሊ ትሪፖሊ ከሽንፈት ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

home-1467096452_supporters-young-africans-tanzanie_1467096452_1467096452

የአንደኛ መርሃግብር ውጤቶች

ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 3-1 ሚዲአማ (ጋና)

ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ) 1-0 ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ)

ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ) 2-1 ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ)

ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ) 1-0 አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ)

ቀጣይ ጨዋታዎች

ማክሰኞ ሰኔ 22/2008

16፡00 – ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) ከ ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) (ቤንጃሚን ማካፓ ናሽናል ስታዲየም)

22፡00 – አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) ከ ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *