ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 ሀዋሳ ከተማ
46′ አዳነ ግርማ 50′ ራምኬል ሎክ | 83′ ሙሉጌታ ምህረት (ፍቅም)


ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የ2008 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ፊሽካም ተነፍቷል፡፡

ተጨማሪ ሰአት
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

90′ አዳነ ግርማ በግንባሩ በመግጨት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

89′ አዳነ ግርማ ግብ ጠባቂውን አልፎ የመታው ኳስ ቋሚውን ታክኮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
83′
ምንተስኖት አዳነ ወጥቶ ናትናኤል ዘለቀ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!!
83′ ሙሉጌታ ምህረት የፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ፍጹም ቅጣት ምት
82′
አስቻለው ታመነ መዳህኔ ታደሰን ጎትቶ በመጣሉ የፍፁም ቅጣት ምት ለሀዋሳ ተሰጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
78′
ግርማ በቀለ ወጥቶ መላኩ ወልዴ ገብቷል፡፡

75′ ጋዲሳ መብራቴ ከቀኝ መስመር ወደ ውስጥ በመግባት የሞከረውን ኳስ ኦዶንካራ ይዞበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
73′
ራምኬል ሎክ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡

67′ ሳላዲን ሰኢድ ከተስፋዬ ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ የሞከረው ኳስ ወደ ወጪ ወጥቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
66′
ምንያህል ተሾመ ወጥቶ ሳለላዲን ሰኢድ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ሀዋሳ
66′
ታፈሰ ሰለሞን ወጥቶ ኤፍሬም ዘካርያስ ገብቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
64′
ተስፉ ኤልያስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

61′ አዳነ ግርማ የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ጎልልል!!!!
50′ ራምኬል ሎክ ግብ ጠባቂውን አልፎ የጊዮርጊስን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ጎልልል !!!!
46′ አዳነ ግርማ ከበሃይሉ አሰፋ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ::

የእረፍት ሰአት የተጫዋች ለውጥ
በረከት ይስሃቅ ወጥቶ አንተነህ ተሻገር ገብቷል፡፡


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ ተጠናቋል፡፡

40′ መድሃኔ ሳጥን ውስጥ የሞከረውን ኳስ ኦዶንካራ መልሶታል፡፡

32′ ሀይማኖት ወርቁ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ኦዶንካራ ይዞታል፡፡

28′ ሜዳው ቃላት ከሚገልፀው በላይ ጨቅይቶ ለመጫወት አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

22′ አዳነ ግርማ ከርቀት የመታው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

18′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ አዳነ በግንባሩ ገጭቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

18′ በሃይሉ አሰፋ ነፃ ኳስ ቢያገኝም የመታውን ኳስ ግርማ ተንሸራቶ አውጥቶታል፡፡

16′ ጋዲሳ መብራቴ ከቀኝ መስመር የመታውን ኳስ ኦዶንካራ በቀላሉ ይዞታል፡፡

15′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ሙከራዎች እስካሁን አልተስተናገዱም፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በሀዋሳ ከተማ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

30 ሮበርት ኦዶንካራ

15 አስቻለው ታመነ – 12 ደጉ ደበበ (አምበል) – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 4 አበባው ቡታቆ

21 ተስፋዬ አለባቸው – 23 ምንተስኖት አዳነ

17 ራምኬል ሎክ – 9 ምንያህል ተሾመ – 7 በሃይሉ አሰፋ

19 አዳነ ግርማ

ተጠባባቂዎች
22 ዘሪሁን ታደለ
3 መሃሪ መና
26 ናትናኤል ዘለቀ
11ዳዋ ሁቴሳ
14 አለማየሁ ሙለታ
20 ዘካሪያስ ቱጂ
10 ሳላዲን ሰኢድ


የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ

84 ዮሃንስ በዛብህ

2 ግሩም አሰፋ – 8 ግርማ በቀለ – 17 ሙጂብ ቃሲም – 18 ተስፉ ኤልያስ

24 ሃይማኖት ወርቁ – 21ሙሉጌታ ምህረት (አምበል)
10 በረከት ይስሃቅ – 5 ታፈሰ ሰሎሞን – 11 ጋዲሳ መብራቴ

15 መድሃኔ ታደሰ

ተጠባባቂዎች
1 ክብረአብ ዳዊት
6 አዲስአለም ተስፋዬ
22 መላኩ ወልዴ
19 ዮሐንስ ሰገቦ
4 አስጨናቂ ሉቃስ
9 አንተነህ ተሻገር
3 ኤፍሬም ዘካርያስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *