01:40 ደጉ ደበበ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አንስቷል፡፡
01:35 በአሁኑ ሰአት የቅዱስ ጊዮርጊስ አባላት ወደ ሽልማት መስጫው እያመሩ ይገኛሉ፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጁነይዲ ባሻ ሜዳልያ እየሸለሙ ይገኛሉ፡፡
ቻምፒዮን
ቅዱስ ጊዮርጊስ የዋንጫ ፣ ወርቅ ሜዳልያ እና 150000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
2ኛ ደረጃ
ኢትዮጵያ ቡና የ100000 ብር እና የብር ሜዳለልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
01:34 ቀጣይ ሸላሚ አቶ ተክለወይኒ ናቸው፡፡
3ኛ ደረጃ
አዳማ ከተማ የ75000 ብር እነና የነሀስ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ አሰልጣኝ አሸናፊ ሽልማቱን ተረክበዋል፡፡
01:32 አቶ አለማየሁ ሀይሌ ቀጣይ ሸላሚ ናቸው
የስፖርታዊ ጨዋነት ተሸላሚ
መከላከያ የስፖርታዊ ጨዋነት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ልዩ ሽልማት
ሙሉጌታ ምህረት ልዩ ተሸላሚ ተብሎ የ10000 ብር ሽልማት በአቶ አለማየሁ ገላጋይ አማካኝነት ተሸልሟል፡፡
ኮከብ አሰልጣኝ
ማርት ኑይ የአመቱ ኮከብ አሰልጣኝ ተብለው የ25000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
ኮከብ ተጫዋች
አስቻለው ታመነ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ 25 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ኮከብ ግብ አግቢ
ታፈሰ ተስፋዬ በ15 ግቦች የአመቱ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ በመሆን የ25 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ኮከብ ግብ ጠባቂ
ሮበርት ኦዶንካራ የአመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ ተብሎ የ15000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
01:20 አቶ አሊሚራ መሃመድ የኮከቦች ሽልማት ይሰጣሉ፡፡
ኮከብ ረዳት ዳኛ
ክንዴ ሙሴ የአመቱ ኮከብ ረዳት ዳኛ ተብሎ የ8000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ኮከብ ዳኛ
በላይ ታደሰ የአመቱ ምርጥ ዳኛ ተብሎ 10000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
01:16 ለእለቱ ዳኞች አቶ አለማየሁ ገላጋይ የወርቅ ሜዳልያ አበርክተዋል፡፡
01:15 ኢንጂነር ቾል ቤል ሊጉ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሽልማት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ ፣ አአ ፖሊስ ፣ ጠብታ አምቡላንስ ፣ የአአ ትራፊክ ፖሊስ ፣ የአበበ ቢቂላ ስታድየም አስተዳደር የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
01:11 የመድረክ ስራ ተጠናቆ የክብር እንግዶች ወደ መድረኩ እየመጡ ይገኛሉ፡፡
12:48 በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ መካከል የተካሄደው ጨዋታ ተገናቋል፡፡ የ2008 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ፊሽካም ተነፍቷል፡፡ በአሁኑ ሰአት ሜዳው ላይ የዋንጫ ስነስርአት የሚካሄድበት ጊዜያዊ መድረክ እየተሰራ ይገኛል፡፡
11:30 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዋንጫውን ወደ ቦታው በማምጣት አስቀምጠዋል፡፡
የ2008 የውድድር ዘመን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቻምፒዮንነት ከደቂቃዎች በፊት ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡ የዋንጫ እና የኮከቦች ሽልማት ስነ-ስርአትም ከደቂቃዎች በኀላ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ይህንን ስነስርአት ከአዲስ አበባ ስታድየም በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡