የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሊጉ ድንቅ አቋም ላሳዩ ተጫዋቾች ሽልማት መሰጠት የጀመረው በ1977 አም. ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍ የኮከብ ተጫዋቾችን ዝርዝር እና ተያያዥ እውነታዎችን እናቀርባለን፡፡
የመጀመርያው ኮከብ
ይህ ሽልማት በ1977 መሰጠት ሲጀምር የመጀመርያውን ሽልማት በማግኘት ባለታሪክ የሆነው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተከላካይ ዳኛቸው ደምሴ ነበር፡፡
ሽልማቱን ከአንድ ጊዜ በላይ ያሳኩ ተጫዋቾች
በ31 አመታት የኮከብ ተጫዋች ምርጫ ታሪክ ሽልማቱን ከአንድ ጊዜ በላይ በመውሰድ ባለታሪክ የሆኑት የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሙሉጌታ ከበደ ፣ የኢትዮጵያ ቡናው አሸናፊ ግርማ ፣ ጌታነህ ከበደ (በደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት) ፣ የኤሌክትሪኩ አንዋር ሲራጅ እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ደጉ ደበበ ሲሆኑ ሁለት ጊዜ ሽልማቱን ማንሳት ችለዋል፡፡
አንዋር ሲራጅ
አንዋር ሲራጅ ሊጉ በ1990 በአዲስ መልኩ ከመጀመሩ በፊት እና በኋላ ሽልማቱን የወሰደ ብቸኛ ተጫዋች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የቀድሞው የኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ በ1989 እና 1992 የኮከብ ተጫዋችነት ክብርን ተቀዳጅቷል፡፡
ብቸኛው ግብ ጠባቂ
የመከላከያው ግብ ጠባቂ ጀማል ጣሰው በ31 አመት ታሪክ ሽልማቱን ያገኘ ብቸኛው ግብ ጠባቂ ነው፡፡ ጀማል ጣሰው ሽልማቱን ያገኘው በ2002 በደደቢት ማልያ ነበር፡፡
ጣምራ ሽልማት
ሙሉጌታ ከበደ ፣ ማትያስ ሃይለማርያም ፣ አዳነ ግርማ ፣ ጌታነህ ከበደ እና ኡመድ ኡኩሪ በአንድ አመት የኮከብ ተጫዋችነት እና ኮከብ ግብ አስቆጣሪነት ሽልማትን በጣምራ በመውሰድ ባለ ታሪክ ናቸው፡፡ አህመድ ጁንዲ ፣ ታፈሰ ተስፋዬ እና አሸናፊ ሲሳይ በተመሳሳይ አመት ባይሆንም በተለያዩ ጊዜያት ሁለቱንም ሽልማቶች ማግኘት ችለዋል፡፡
በርካታ ተጫዋች ያስመረጡ ክለቦች
ከ31 ሽልማቶች ቅዱስ ጊዮርጊስ 13 ጊዜ በማስመረጥ ቀዳሚ ሲሆን ኤሌክትሪክ 5 ጊዜ በማስመረጥ ሁለተኛ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ቡና እና ምድር ጦር ደግሞ 3 ጊዜ ማስመረጥ ችለዋል፡፡
አስቻለው ታመነ – 25ኛው ተጫዋች
የዘንድሮው የውድድር ዘመን ኮብ ተጫዋች አስቻለው ታመነ ሽልማቱን ያገኘ 25ኛው ተጫዋች ለመሆን በቅቷል፡፡
ለትውስታ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ1990 በአዲስ መልክ ከተጀመረ ወዲህ ኮከብ ተጫዋች ተብለው የተመረጡት ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡፡
1990.አንዋር ያሲን (ኤሌክትሪክ)
1991.አህመድ ጁንዲ (ምድር ባቡር)
1992.አንዋር ሲራጅ (ኤሌክትሪክ)
1993.አሸናፊ ግርማ (ኢትዮጵያ ቡና)
1994.ሙሉአለም ረጋሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1995.አሸናፊ ግርማ (ኢትዮጵያ ቡና)
1996.ሙሉጌታ ምህረት (ሀዋሳ ከተማ)
1997.ደጉ ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1998.ቢንያም አሰፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
1999 –
2000.ታፈሰ ተስፋዬ (ኢትዮጵያ ቡና)
2001.ጌታነህ ከበደ (ደቡብ ፖሊስ)
2002.ጀማል ጣሰው (ደደቢት)
2003.አዳነ ግርማ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2004.ደጉ ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2005. ጌታነህ ከበደ (ደደቢት)
2006. ኡመድ ኡኩሪ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2007. በሃይሉ አሰፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
2008. አስቻለው ታመነ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)