የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ሁለተኛ መርሃ ግብር ረቡዕ ምሽት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ሲጠናቀቁ ዋይዳድ ካዛብላንካ እና ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ድል ቀንቷቸዋል፡፡ ዋይዳድ ዜስኮ ዩናይትድን 2-0 ሲረታ የደቡብ አፍሪካው ቻምፒዮን ማሜሎዲ ሰንዳውንስ የኢኒምባን የግማሽ ፍፃሜ ጉዞ አደጋ ውስጥ ከቷል፡፡
በሞሮኮ መዲና ራባት በተደረገው የዋይዳድ ካዛብላንካ እና ዜስኮ ዩናይትድ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው የፊፋ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ እና ረዳቶቹ ክንዴ ሙሴ እና ተመስገን ሳሙኤል ዳኝተዋል፡፡ ክንዴ ሙሴ ትላንት በተጠናቀቀው የ2008 የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ኮከብ ረዳት ዳኛ በመባል መሸለሙ ይታወሳል፡፡ የዋይዳድ ፍፁም የሆነ የበላይነት በታየበት ጨዋታ ዋሊድ ኤል ካርቲ ከኢስማኤል ኤል ሃዳድ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ በ12ኛው ደቂቃ የካዛብላንካውን ክለብ መሪ ማድረግ ችሏል፡፡ በተደጋጋሚ የዜስኮን የግብ ክልል ሲፈትኑ የነበሩት ዋይዳዶች በ52ኛው ደቂቃ ኬንያዊው ኢንተርናሽናል ዴቪድ ኦዊኖ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ አሸንፈው መውጣጥ ችለዋል፡፡ ሽንፈቱን ተከትሎ ዜስኮ ዩናይትድ አል አሃሊን ማሸነፍ ከቻለው አሴክ ሚሞሳስ በግብ ክፍያ ተበልጦ በ3 ነጥብ ሶስተኛ ሲሆን ዋይደድ በስድስት ነጥብ የምድቡን መሪነት አጠናክሯል፡፡
ፕሪቶሪያ ላይ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ኢኒምባን 2-1 በመርታት የግማሽ ፍፃሜ ጉዟቸውን መስመር ሲያሲዙ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን የተሸነው ኢኒምባ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ኮሎምቢያዊው ሊዮናርዶ ካስትሮ የኢኒምባን ተከካላካዮች መዘናጋት ተጠቅሞ ብራዚሎቹን ቀዳሚ ሲያደርግ ሞሰስ ኦጆ በሁለተኛው አጋማሽ በድንቅ ሁኔታ ከረጅም ርቀት ኳስ እና መረብ በማገናኘት አቻ ማድረግ ችሏል፡፡ ዋይን አርንደስ የሰንዳውንስን የድል ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ ምድብ ሁለትን ማሜሎዲን ሰንዳውን በሶስት ነጥብ ሲመራ ዛማሌክ በዕኩል ነጥብ ይመራል፡፡ ኢኒምባ የምድቡን ግርጌ ይዛል፡፡ የኢኤስ ሴቲፍን መቀጣት ተከትሎ በምድቡ ሶስት ክለቦች ብቻ በመቅረታቸው የኢኒምባን የማልለፍ ተስፋ ከወዲሁ መጨለም ጀምሯል፡፡
ውጤቶች
አል አሃሊ (ግብፅ) 1-2 አሴክ ሚሞሳስ (ኮትዲቯር)
ዋይዳድ ክለብ አትሌቲክ (ሞሮኮ) 2-0 ዜስኮ ዩናይትድ (ዛምቢያ)
ማሜሎዲ ሰንዳውንስ (ደቡብ አፍሪካ) 2-1 ኢኒምባ ኢንተርናሽል (ናይጄሪያ)