ኮንፌዴሬሽን ካፕ ፡ ሚዲአማ እና ኤቷል ደ ሳህል በሜዳቸው ነጥብ ጥለዋል

በኦሬንጅ ካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች መርሃግብር ትላንት በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡ ሚዲአማ ከኤምኦ ቤጃያ ጋር ያለግብ አቻ ሲወጣ የ2015ቱ ኮንፌድሬሽን ካፕ አሸናፊ ኤቷል ደ ሳህል እና ፉስ ራባት 1-1 ተለያይተዋል፡፡

ሚዲአማ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ጠንካራውን የቤጃያ የተከላካይ ስፍራ ማስከፍት ሰይችል በሜዳው አቻ ወጥቷል፡፡ በኮንፌድሬሽን ካፕ ጨዋታዎች ምክንያት ከፍተኛ ፋይናንስ ቀውስ ውስጥ የገባው ሚዲአማ በተደጋጋሚ የቤጃያን የተከላካይ ክፍል ቢፈትንም ግብ ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል፡፡ ቤጃያ ጥብቅ የመከላከል ተክቲክን የተጠቀመ ሲሆን የሚፈልጉትን ውጤት ይዘው ወደ አልጄሪያ እንዲመለሱ አስችሏቸዋል፡፡ የሚዲአማ ባለበት የፋይናንስ ቀውስ ምክንያት ከውድድሩ እራሱን ለማግለል እያሰበ እንደሆነ ከጋና የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡  በምድብ አንድ ቤጃያ በአራት ነጥብ ቲፒ ማዜምቤን ተከትሎ ሁለተኛ ሲሆን ሚዲአማ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ነው፡፡

PicsArt_1467278047610

በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ሶስ ላይ የቱኒዚያ ሻምፒዮን እና የሞሮኮ ሻምፒዮን ሲያገናኝ ፉስ ራባት ወሳኝ የሆነ አንድ ነጥብ መያዝ ችሏል፡፡ ከሽንፈት ለመመለስ ለጨዋታው ሰፊ ትኩረት የሰጡት ኤቷል ደ ሳህሎች ሶስት ነጥብ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡ አህመድ አኪያቺ ኤቷልን ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም አቡዱልሰላም ቤን ዣሉን ለራባቱ ክለብ የአቻቷን ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡ የአቻ ውጤቱን ተከትሎ ፉስ በአራት ነጥብ የምድብ ሁለትን ሁለተኛነት ሲያስጠብቅ ኤቷል በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ነው፡፡

PicsArt_1467278066739

ውጤቶች

ያንግ አፍሪካንስ (ታንዛኒያ) 0-1 ቲፒ ማዜምቤ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

ሚዲአማ (ጋና) 0-0 ሞሊዲያ ኦሎምፒክ ቤጃያ (አልጄሪያ)

አል አሃሊ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 1-2 ካውካብ አትሌቲክ ክለብ ማራካሽ (ሞሮኮ)

ኤቷል ስፖርቲቭ ደ ሳህል (ቱኒዚያ) 1-1 ፋት ዩኒየን ስፖርት ራባት (ሞሮኮ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *