ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አርባምንጭ ከተማ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 3-2 አርባምንጭ ከተማ
62′ ሳላዲን ሰኢድ 83′ 90+3′ አዳነ ግርማ | 32′ አማኑኤል ጎበና 71′ ተሾመ ታደሰ


ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ 3-2 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡ አዳነ ግርማ የአርባምንጭን መሪነት ቀልብሶ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸናፊ አድርጓል፡፡

ጎልልል!!!!
90+3′ አዳነ ግርማ ወደ ግብ ያሻማው ኳስ ሲመለስ በቮሊ ግሩም ግብ አስቆጥሯል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
90′
ፍሬዘር ካሳ ወጥቶ መሃሪ መና ገብቷል፡፡

85′ ተስፋዬ አለባቸው አማኑኤል ላይ በሰራው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ቢጫ ካርድ
84′
አይዛክ ኢዜንዴ ከጨዋታ ውጪ በመመታቱ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!!
83′ አዳነ ግርማ በግንባሩ በመግጨት አስቆጥሮ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡ ወደ አርባምንጭ ደጋፊዎች በመሄድም ደስታውን ገልጿል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ጊዮርጊስ
78′
ናትናኤል ዘለቀ ወጥቶ ምንተስኖት አዳነ ገብቷል፡፡

77′ አዳነ ግርማ በክርን በመማታቱ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጸጋዬ ከአርቢቴር በአምላከ ጋር ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው በቀይ ካርድ ከመቀመጫቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡

76′ የአርባምንጭ ደጋፊዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች ላይ ጸያፍ ስድብ እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡

ቢጫ ካርድ
75′
ወርቅይታደል እና አመለ ሚልኪያስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – አርባምንጭ
75′
ተሾመ ታደሰ ወጥቶ በረከት ቦጋለ ገብቷል፡፡

ጎልልል!!!!
71′ ተሾመ ታደሰ ከአመለ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ አርባምንጭን በድጋሚ መሪ አድርጓል፡፡

67′ አዳነ ግርማ በግራ እግሩ አክርሮ የመታውን ኳስ አንተነህ መሳ መልሶታል፡፡

ጎልልል!!!!
62′ ሳላዲን ሰኢድ በተከላካይ እና ግብጠባቂ መካከል የነበረውን አለመግባባት ተጠቅሞ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡

50′ ታደለ መንገሻ ከርቀት የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

49′ በሃይሉ አሰፋ ከቀኝ መስመር አክርሮ የመታውን ኳስ አንተነህ ይዞበታል፡፡

ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀመረ::


እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአርባምንጭ መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
40′
ራምኬል ሎክ (ጉዳት) ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡

35′ ሳላዲን ሰኢድ የግብ ጠባቂውን መውጣት ተመልክቶ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

33′ በሃይሉ አሰፋ ያሻገረለትን ኳስ አዳነ ሞክሮ ወደ ውጢ ወጥቶበታል፡፡

ጎልልል!!!! አርባምንጭ
32′ አማኑኤል ጎበና ከመሃል ሜዳ ወደ ግብ በመገስገስ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ወደ ግብነት ለውጦታል፡፡

10′ አርባምንጭ ከተማዎች ወደ ጊዮርጊስ የግብ ክልል በተደጋጋሚ በመቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

5′ አበባው ቡታቆ ከርቀት የሞከረው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

1′ ጸጋዬ አበራ በቮሊ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!!
ጨዋታው በአርባምንጭ አማካኝነት ተጀምሯል፡፡


የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ

22 ዘሪሁን ታደለ

15 አስቻለው ታመነ – 2 ፍሬዘር ካሳ – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 4 አበባው ቡታቆ

21 ተስፋዬ አለባቸው – 26 ናትናኤል ዘለቀ

17 ራምኬል ሎክ – አዳነ ግርማ (አምበል) – 7 በሃይሉ አሰፋ

10 ሳላዲን ሰኢድ

ተጠባባቂዎች
30 ሮበርት ኦዶንካራ
3 መሃሪ መና
23ምንተስኖት አዳነ
11ዳዋ ሁቴሳ
14 አለማየሁ ሙለታ
20 ዘካሪያስ ቱጂ
12 ደጉ ደበበ

የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

1 አንተነህ መሳ

2 ወርቅይታደል አበበ – 12 ቢያድግልኝ ኤልያስ – 4 አበበ ጥላሁን – 13 ጸጋዬ አበራ

8 ትርታዬ ደመቀ – 18 አማኑኤል ጎበና (አምበል) – 21 ምንተስኖት አበራ – 17 ታደለ መንገሻ

11አመለ ሚልኪያስ – 23 ተሾመ ታደሰ

ተጠባባቂዎች
70 ጌድዮን መርዕድ
3 ታገል አበበ
16 በረከት ቦጋለ
10 መልካሙ ፉንዱሬ
6 ታሪኩ ጎጀሌ
19 ገብረሚካኤል ያዕቆብ
11 ተመስገን ዱባ

Leave a Reply