” ዋንጫውን በማጣታችን ብከፋም ኮከብ ሆኜ በመመረጤ ከሚገባው በላይ ተደስቻለሁ ” ሽታዬ ሲሳይ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ትላንት በደደቢት አሸናፊነት ሲጠናቀቅ የንግድ ባንኳ አጥቂ ሽታዬ ሲሳይ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተመርጣለች፡፡

ሽታዬ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠችው አስተያየት ንግድ ባንክ በፍፃሜው በመሸነፉ የኮከብ ተጫዋቾነቱን እንዳልጠበቀችው ተናግራለች፡፡

” በኮከብነት እመረጣለሁ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር፡፡ ያው ከአሸናፊ ቡድን ብዙ ጊዜ ይመረጣል ስለሚባል እመረጣለው ብዬ አልገመትኩም፡፡ ሆኖም በሀዋሳው ውድድር ላይ ካሳየሁት ብቃት አንጻር ኮከብነቱን አግኝቻለሁ፡፡ ከዞኑ ውድድር በተሻለ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርጌያለሁ፡፡” ብላለች፡፡ ሽታዬ ኮከብነቱን ባትጠብቀውም በመሸለሟ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማት ገልፃለች፡፡

” እጅግ በጣም ነው ደስ ብሎኛል፡፡ ዋንጫውን በማጣታችን ደስተኛ ባልሆንም በግሌ ኮከብ ሆኜ በመመረጤ ከሚገባው በላይ ደስ ብሎኛል፡፡ ”

PicsArt_1467540176959

ሽታዬ ሲሳይ ከክለቧ ጋር የለመደችውን ዋንጫ ዘንድሮ ማሳካት አልቻለችም፡፡ የከፍተኛ ግብ አግቢነቱንም ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ በሎዛ አበራ ተቀድማለች፡፡ ያጣቻቸውን ክብሮች በቀጣይ አመት ለማግኘት ጠንክራ እንደምትሰራ ተናግራለች፡፡

” ከአሁን በኃላ የተወሰነ እረፍት አድርጌ ጠንካሬ እሰራለሁ፡፡ ለቀጣዩ የውድድር ዘመን በግሌ ያለብኝን ድከመት በሚገባ አሻሽዬ እና ዝግጁ ሆኜ እመጣለው፡፡ ክለቤ ያጣውን ዋንጫ እንዲሁም የኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱንም ማሳካት እፈልጋለው”

 

Leave a Reply