በኢትዮዽያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ውድድር ትላንት በተደረጉ አራት የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉ ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል፡፡
ቦዲቲ ላይ ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ጨዋታ በመደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ በመጠናቀቁ በተሰጠው የመለያ ምት ወላይታ ድቻ 5-3 ማሸነፍ ችሏል፡፡
ጎፋ በሚገኘው የኤሌክትሪክ በተደረጉ ጨዋታዎች ኢትዮዽያ ቡና መከላክያን 1-0 ሲረታ ኤሌትሪክ በአፍሮ ፅዮን 2-1 ተሸንፏል፡፡
ሐዋሳ ላይ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ተመልካች በተገኘበትና ማራኪ የኳስ እንቅስቃሴ በታየበት ጨዋታ ሁለቱን የዞን ቻምፒዮኖች ሀዋሳ ከተማ እና ደደቢትን አገናኝቶ ሀዋሳ ከተማዎች ከእረፍት መልስ ባስቆጠሩት ብቸኛ ጎል አሸንፈዋል፡፡
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች
ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ
አፍሮ ፅዮን ከ ከሀዋሳ ከተማ
(የጨዋታዎቹ ቦታ፣ ቀን እና ሰአት ወደፊት ይገለፃል)