በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ደደቢት ሴፋክሲያንን ያስተናግዳል

በ2014 የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የዛንዚባሩን ኬኤምኬኤምን በድምር ውጤት 3-2 አሸንፎ ወደ ተከታዩ ዙር ያለፈው ደደቢት በ1ኛው ዙር የአምናውን የአፍሪካ ኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ አሸናፊ ስፖርትስ ሴፋክሲያንን እሁድ በ10፡00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናግዳል፡፡

የቱኒዚያው ክለብ ከአፍሪካ ታላላቅ ክለቦች ውስጥ የሚመደብ ሲሆን በአፍሪካ ክለቦች ደረጃ መሰረት ቱኒዚያ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በመገኘቷ ሴፋክሲያን ያለ ቅድመ ማጣርያ ወደ 32 ቡድኖች በቀጥታ አልፏል፡፡

ደደቢት ባለፈው ሃሙስ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ካደረገ በኃላ በእረፍት ላይ ሲሆን በፌዴሬሽኑ ውሳኔ ከወላይታ ድቻ ጋር ሊያደርገው የነበረው ፍልሚያ ለሌላ ቀን መተላለፉን ተከትሎ ጠንካራ ልምምድ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፡፡

ደደቢት በቅድመ ማጣርያው በኬኤምኬኤም ከባድ ፈተና ውስጥ የገባ ሲሆን ይህም ጨዋታ እጅግ ፈታኝ ይሆንበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ሴፋክሲያን አምና በኮንፌድሬሽንስ ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ቅዱስ ጊዮርጊስን አዲስ አበባ ላይ 3-1 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ