አዳማ ከተማ 1-1 (4-5) ቅዱስ ጊዮርጊስ
61′ ሱሌማን መሃመድ | 40′ ሳላዲን ሰኢድ (ፍቅም)
ተጠናቀቀ
በመለያ ምት ቅዱስ ጊዮርጊስ 5-4 አሸንፎ ሀሙስ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ አልፏል፡፡
5ኛ ምት – አዳነ ግርማ ለጊዮርጊስ አስቆጠረ፡፡ 4-5
5ኛ ምት – ሞገስ ታደሰ ሳተ፡፡ 4-4
4ኛ ምት – አበባው ቡታቆ ለጊዮርጊስ አስቆጥሯል፡፡ 4-4
4ኛ ምት – እሸቱ መና ለአዳማ አስቆጥሯል፡፡ 4-3
3ኛ ምት – አስቻለው ታመነ ለጊዮርጊስ አስቆጥሯል፡፡ 3-3
3ኛ ምት – ሚካኤል ጆርጅ ለአዳማ አስቆጥሯል፡፡ 3-2
2ኛ ምት – ምንተስኖት አዳነ ለጊዮርጊስ አስቆጥሯል፡፡ 2-2
2ኛ ምት – ብሩክ ቃልቦሬ ለአዳማ አስቆጥሯል፡፡ 2-1
የመጀመርያ ምት – ሳላዲን ሰኢድ ለጊዮርጊስ አስቆጥሯል፡፡ 1-1
የመጀመርያ ምት – ታፈሰ ተስፋዬ ለአዳማ አስቆጥሯል ፡፡ 1-0
ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ:: አሸናፊውን ለመለየት ወደ መለያ ምት ያመራሉ፡፡
ተጨማሪ ደቂቃ
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
90′ ዘካርያስ ቱጂ ወጥቶ አበባው ቡታቆ ገብቷል፡፡
88′ የአዳማ ከተማ ደጋፊዎች ባማረ ህብረ ዝማሬ ቡድናቸው ጎል እዲያስቆጥር እያነሳሱ ይገኛሉ፡፡
84′ ሚካኤል ጆርጅ በአክሮባቲክ ምት የሞከረው ኳስ ተጨርፎ ወጣበት፡፡ ግሩም ሙከራ !
የተጫዋች ለውጥ – አዳማ
82′ ሱሌማን መሃመድ ወጥቶ ዮናታን ከበደ ገብቷል፡፡
80′ አዳማ በፍፁም የበላይነት ጨዋታውን ተቆጣጥሮ ሲጫወት ፈረሰኞቹ ከጨዋታው እንቅስቃሴ ውጭ ሆነዋል ማለት ይቻላል፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
77′ በኃይሉ አሰፋ ወጥቶ ዳዋ ሁቴሳ ገብቷል፡፡
77′ በድጋሚ ሚካኤል ጆርጅ ግልፅ የማግባት አጋጣሚ አምክኗል፡፡
75′ ዲሚጥሮስ ከመስመር መሬት ለመሬት ያሻገረውን ግልጽ የማግባት አጋጣሚ ታከለ አለማየሁ ለማመን በሚከብድ ሆኔታ ስቶታል፡፡
72′ አዳማ ከተማ ሙሉ ለሙሉ የእንቅስቃሴ ብልጫ ወስዶ እየተጫወተ ይገኛል፡፡
70′ ታፈሰ ተስፋዬ በግምት ከ17 ሜትር ርቀት የተገኘውን ቅጣት ምት ሞክሮ በግቡ አናት ለጥቂት ወጥቶበታል፡፡
የተጨዋች ለውጥ – አዳማ
67′ ተስፋዬ በቀለ ወጥቶ ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ ገብቷል፡፡
64′ ታፈሰ ተስፈዬ ግቅ አስቆጥሮ ደስታውን በዳንስ ቢያሳይም የዕለቱ ረዳት ዳኛ ከጨዋታ ውጪ በማለታቸው ጎሉ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡ የአዳማ ተጨዋቾች የዕለቱን ዳኛ በመክበብ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡
ጎልልል!!!!
61′ ሱሌማን በግራ መስመር ያሻገረው ኳስ በቀጥታ ወደ ግብነት ተቀይሮ አዳማ ከተማን አቻ አድርጓል፡፡
60′ አዳማ ወደ ጨዋታው ለመለስ ጫና ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ቢሆንም ፈረሰኞቹ በመልሶ ማጥቃት የአዳማን የተከላካይ ክፍል እየፈተኑ ይገኛሉ፡፡
የተጨዋች ለውጥ – አዳማ ከተማ
52′ ጫላ ድሪባ ወጥቶ ሱራፌል ዳኛቸው ገብቷል፡፡
50′ ጨዋታው ከእረፍት መልስ የተሟሟቀ መልክ ይዟል፡፡
49′ ታፈሰ ተስፋዬ አሁንም መሬት ለመሬት አክሮ የመታውን ዘሪሁን እንደምንም ተወርውሮ አወጥቶበታል፡፡
48′ ሳላዲን ሰኢድ ከግብ ጠባቂው ጋር ተገናኝቶ ቺፕ አድርጎ ለማስቆጠር ሲሞክር ጃኮብ ፔንዛ ይዞበታል፡፡
ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በጊዮርጊስ መሪነት ተጠናቋል፡፡
ተጨማሪ ሰአት
የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
ጎልልል!!!!!
40′ ሳላዲን ሰኢድ የፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡
ፍፁም ቅጣት ምት
39′ ጃኮብ በኃይሉን ገፍቶ ሚዛኑን በማሳቱ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል፡፡ ለቅዱስ ጊዮርጊስም የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል
37′ የስፖርት ቤተሰቡ ጨዋታው 08:00 መሆኑን በመገመት በአሁን ሰአት ወደ ሜዳ በርከት ብለው በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ቢጫ ካርድ
35′ አይዛክ ኢዜንዴ የጨዋታውን የመጀመርያ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
34′ ታፈሰ ተስፋዬ በግምት ከ30 ሜትር ርቀት መሬት ለመሬት አክሮ የመታውን ኳስ ዘሪሁን ወደ ውጭ አውጥቶበታል፡፡
30′ ይህ ነው የሚባል የተሳካ የኳስ ቅብብል የሌለበትና የደበዘዘ ጨዋታ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ የጨዋታው ሰአት ለቡድኖቹ ፈተና የሆነባቸው ይመስላል፡፡
20′ በሁለቱም በኩል አልፎ አልፎ ወደ ጎል ቀጠና ለመግባት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጭ እምብዛም ማራኪ እንቅስቃሴ አልታየም፡፡
13′ ቡሩክ ቃልቦሬ ከ25 ሜትር ርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ ዘሪሁን እንደምንም ያዘበት፡፡ የጨዋታው የመጀመርያ ጠንካራ ሙከራ..
10′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ በሁለቱም በኩል ለጎል የቀረበ ሙከራ አልተደረገም፡፡
ተጀመረ!
ጨዋታው በአዳማ ከተማ አማካኝነት ተጀመረ፡፡
07:09 ሁለቱ ቡድኖች ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡
07:00 ወከባና ግርግር ፣ ከፍተኛ ጥበቃ ፣ ስጋት ፣ በዝምታ የተዋጠ ሜዳ ፣ አነስተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች . . . . ከጨዋታው በፊት ያለው ገፅታ ይህን ይመስላል፡፡
እንደ ውድድሩ ወሳኝነት በአዳማ አበበ በቂላ ስቴዲዮም የተገኘው ተመልካች ከወትሮው እጅግ አነስተኛ ነው፡፡
የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
1 ጃኮብ ፔንዛ
6 እሸቱ መና – 20 ሞገስ ታደሰ – 5 ተስፋዬ በቀለ – 11 ሱሌማን መሃመድ (አምበል)
7 ታከለ አለማየሁ – 8 ብሩክ ቃለቦሬ – 19 ፋሲካ አስፋው – 15 ጫላ ድሪባ
9 ሚካኤል ጆርጅ – 21 ታፈሰ ተስፋዬ
ተጠባባቂዎች
99 ጃፋር ደሊል
3 ዲሚጥሮስ ወልደስላሴ
4 ወንድወሰን ሚልኪያስ
16 ዮናታን ከበደ
18 ሻኪሩ ኦላዴ
80 ሱራፌል ዳኛቸው
26 ያሬድ ዘውድነህ
የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ
22 ዘሪሁን ታደለ
15 አስቻለው ታመነ – ደጉ ደበበ (አምበል) – 5 አይዛክ ኢዜንዴ – 3 መሃሪ መና
23 ምንተስኖት አዳነ – 26 ናትናኤል ዘለቀ
20 ዘካርያስ ቱጂ – አዳነ ግርማ – 7 በሃይሉ አሰፋ
10 ሳላዲን ሰኢድ
ተጠባባቂዎች
1ፍሬው ጌትነት
2 ፍሬዘር ካሳ
4 አበባው ቡታቆ
6 አሉላ ግርማ
11ዳዋ ሁቴሳ
14 አለማየሁ ሙለታ
18 አቡበከር ሳኒ